ሐዋርያት ሥራ 25:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊቃነ ካህናትና የአይሁድ ሽማግሎችም ከበቡት፤ የጳውሎስንም ነገር ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህናት አለቆችና የአይሁድ መሪዎች ፊቱ ቀርበው ጳውሎስን ከሰሱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካህናቱ አለቆችና የአይሁድም ታላላቆች በጳውሎስ ላይ አመለከቱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም የካህናት አለቆችና አንዳንድ ታላላቅ የአይሁድ ወገኖች በጳውሎስ ላይ ክሳቸውን አቀረቡ፤ “ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም በማስመጣት ለእኛ መልካም ነገር አድርግልን” ሲሉም ለመኑት፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ጳውሎስን በመንገድ ጠብቀው ሊገድሉት ስለ ፈለጉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካህናቱ አለቆችና የአይሁድም ታላላቆች በጳውሎስ ላይ አመለከቱ፥ |
በአምስተኛውም ቀን ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከመምህራኑና ጠርጠሉስ ከሚባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳውሎስንም በአገረ ገዢው ዘንድ ከሰሱት።
ፊስጦስም እንዲህ አለ፥ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ወንድሞቻችን ሁላችሁ፥ ስሙ፤ አይሁድ ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንዳይገባው በኢየሩሳሌምም ሆነ በዚህ እየጮሁ የለመኑኝ ይህ የምታዩት ሰው እነሆ።
ከሦስት ቀንም በኋላ ጳውሎስ የአይሁድን ታላላቅ ሰዎች ሰበሰባቸው፤ በተሰበሰቡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፥ “ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔ በሕዝቡም ላይ ቢሆን፥ በአባቶቻችንም ሕግ ላይ ቢሆን ያደረግሁት ክፉ ነገር የለም፤ ነገር ግን በኢየሩሳሌም እንደ ታሰርሁ ለሮም ሰዎች አሳልፈው ሰጡኝ።