ሐዋርያት ሥራ 20:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድካማችንና በሥራችን ነዳያንን እንቀበላቸው ዘንድ እንደሚገባን ይህን አስተምሬአችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለውንም የጌታችንን የኢየሱስን ቃል ዐስቡ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጕልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ምስጉን ነው’ ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው፤’ እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው’ የሚለውን የጌታ ኢየሱስን ቃል በማስታወስ፥ በእጃችን እየሠራን ደካሞችን መርዳት እንደሚገባን በብዙ መንገድ አሳይቻችኋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፦ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ። |
በእኛ ሹመት ሌላ የሚቀድመን ከሆነ የሚሻላችሁን እናንተ ታውቃላችሁ፤ እኔ ይህን አልፈለግሁትም፤ ነገር ግን የክርስቶስን ትምህርት እንዳላሰናክል በሁሉ እታገሣለሁ።
ነገር ግን ያደረግሁትም ቢሆን፥ የማደርገውም ቢሆን፥ እነርሱ እንደ እኛ የሚመኩበትን ያገኙ ዘንድ፥ ምክንያት የሚሹትን ምክንያት አሳጣቸው ዘንድ ነው።
ከእናንተ ዘንድ በነበርሁበት ጊዜም፥ ስቸገር ገንዘባችሁን አልተመኘሁም። ባልበቃኝም ጊዜ ወንድሞቻችን ከመቄዶንያ መጥተው አሙአሉልኝ፤ በእናንተም ላይ እንዳልከብድባችሁ በሁሉ ተጠነቀቅሁ፤ ወደ ፊትም እጠነቀቃለሁ።
እከብድባችሁ ዘንድ ወደ እናንተ ካለመምጣቴ በቀር፥ ከአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያሳነስኋችሁ በምንድን ነው? ይህቺን በደሌን ይቅር በሉኝ።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸርነቱን ታውቃላችሁ፤ በእርሱ ድህነት እናንተ ባለጸጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለጸጋ ሲሆን፥ ስለ እናንተ ራሱን ድሃ አደረገ።
ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።
ነገር ግን ለድሆች መራራትን፥ ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።
ከእነርሱ ጋር አብራችኋቸው እንደ ታሰራችሁ ሆናችሁ እስረኞችን ዐስቡ፤ መከራ የጸናባቸውንም በሥጋችሁ ከእነሱ ጋር እንዳላችሁ ሆናችሁ ዐስቡ።