እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ቁም፤ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ይሰግዱ ዘንድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ ትነግራቸው ዘንድ ያዘዝሁህን ቃል ሁሉ ተናገራቸው፤ አንዲትም ቃል አታጕድል።
ሐዋርያት ሥራ 20:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጉባኤም ሆነ በቤት ስነግራችሁና ሳስተምራችሁ ከሚጠቅማችሁ ነገር አንዳች ስንኳን አላስቀረሁባችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአደባባይም ሆነ ከቤት ቤት በመዘዋወር፣ እናንተን ከማስተማርና ይጠቅማችኋል ብዬ ያሰብሁትን ከመስበክ ወደ ኋላ አላልሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአደባባይም ሆነ በየቤታችሁ ሳስተምራችሁ የሚጠቅማችሁን ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ፥ ምንም ነገር አላስቀረሁባችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአደባባይም ሆነ በየቤታችሁ ሳስተምራችሁ የሚጠቅማችሁን ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ፥ ምንም ነገር አላስቀረሁባችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ንስሐንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች እየመሰከርሁ በጉባኤም በየቤታችሁም አወራሁላችሁና አስተማርኋችሁ እንጂ፥ ከሚጠቅማችሁ ነገር አንዳች ስንኳ አላስቀረሁባችሁም። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ቁም፤ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ይሰግዱ ዘንድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ ትነግራቸው ዘንድ ያዘዝሁህን ቃል ሁሉ ተናገራቸው፤ አንዲትም ቃል አታጕድል።
ነቢዩ ኤርምያስም አላቸው፥ “ሰምታችኋል፤ እነሆ እንደ ቃላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔርም የሚመልስልኝን ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ ከእናንተም አንድም ቃል አልሸሽግም።”
ሁልጊዜም አንድ ልብ ሆነው በቤተ መቅደስ ያገለግሉ ነበር፤ በቤትም ኅብስትን ይቈርሱ ነበር፤ በደስታና በልብ ቅንንነትም ምግባቸውን ይመገቡ ነበር።
ከሚስቱም ጋራ ተማክሮ የዋጋዉን እኩሌታ አስቀረ፤ የዋጋውንም እኩሌታ አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አስቀመጠ።
ሁልጊዜም በቤተ መቅደስና በቤት ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አልተዉም።
አሁንም ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በማታውቁት ቋንቋ ባነጋግራችሁ፥ የጥበብ ነገርንም ቢሆን፥ የትንቢትንም ነገር ቢሆን፥ የማስተማር ሥራንም ቢሆን ገልጬ ካልነገርኋችሁ የምጠቅማችሁ ጥቅም ምንድን ነው?
እነሆ፥ እናንተ ገብታችሁ በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ዘንድ አምላኬ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ ሥርዐትና ፍርድን አሳየኋችሁ።
እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ፍጹም የሚሆነውን ሰው እናቀርበው ዘንድ፥ እኛ የምናስተምርለት፥ ሰውን ሁሉ ወደ እርሱ የምንጠራለትና የምንገሥጽለት፥ ሥራውንም በጥበብ ሁሉ የምንናገርለት ነው።