Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 12:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ለሁ​ሉም ጌታ እየ​ረዳ በየ​ዕ​ድሉ እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ውና እን​ደ​ሚ​ጠ​ቅ​መው ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ በግ​ልጥ ይሰ​ጠ​ዋል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ሰው የሚሰጠው ለጋራ ጥቅም ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ለእያንዳንዱ የመንፈስን መገለጥ የሚሰጠው ለጥቅም ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ለእያንዳንዱ መንፈስ ቅዱስን የመግለጥ ስጦታ የሚሰጠው ለጋራ ጥቅም ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 12:7
11 Referencias Cruzadas  

አን​ተም የጥ​በብ መን​ፈስ ለሞ​ላ​ሁ​ባ​ቸው፥ በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ለሆ​ኑት ሁሉ ተና​ገር። እነ​ር​ሱም ካህን ሆኖ እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ለአ​ሮን ለቤተ መቅ​ደስ የሚ​ሆን የተ​ለየ ልብስ ይሥሩ፤


አካል አንድ እንደ ሆነ ብዙ የአ​ካል ክፍ​ሎ​ችም እንደ አሉ​በት፥ ነገር ግን የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ብዙ​ዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ ክር​ስ​ቶስ ደግሞ እን​ዲሁ ነው፤


እን​ዲሁ እና​ን​ተም ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ ስጦታ ተፎ​ካ​ከሩ፤ ትበ​ዙም ዘንድ ማኅ​በሩ የሚ​ታ​ነ​ጽ​በ​ትን ፈልጉ።


እነሆ፥ አን​ተስ መል​ካም ታመ​ሰ​ግ​ና​ለህ፤ ነገር ግን ሌላው እን​ዴት ይታ​ነ​ጻል?


ነገር ግን ሌሎ​ችን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በቋ​ንቋ ከሚ​ነ​ገር ብዙ ቃል ይልቅ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በአ​እ​ም​ሮዬ አም​ስት ቃላ​ትን ልና​ገር እሻ​ለሁ።


ሁላ​ች​ሁም በቋ​ንቋ ልት​ና​ገሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ትን​ቢት ልት​ና​ገሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ሳይ​ተ​ረ​ጕም በቋ​ንቋ ከሚ​ና​ገር ይልቅ ትን​ቢት የሚ​ና​ገር እጅግ ይበ​ል​ጣ​ልና፤ ቢተ​ረ​ጕም ግን ማኅ​በ​ሩን ያን​ጻል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos