የሰማይም ከዋክብትና ኦሪዎን፥ የሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ብርሃናቸውን አይሰጡም፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፤ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።
ሐዋርያት ሥራ 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምትገለጠው ታላቅዋ የእግዚአብሔር ቀን ሳትመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታላቁና ክቡር የሆነው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ፀሓይ ወደ ጨለማ፣ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታላቁና አስገራሚው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፥ ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ደም ትመስላለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ። |
የሰማይም ከዋክብትና ኦሪዎን፥ የሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ብርሃናቸውን አይሰጡም፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፤ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።
እነሆ፥ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፥ ኀጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።
ጣራቸው ይፈርሳል፤ ግድግዳቸውም ይወድቃል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ ይነግሣልና፥ በሽማግሌዎቹም ፊት ይከብራልና።
በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይደንግጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና።
“በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም ላይ ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ይጨነቃሉ፤ ከባሕሩና ከሞገዱ ድምፅ የተነሣም ይሸበራሉ።
ሥጋውን ጎድቶ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን ነፍሱ ትድን ዘንድ እንዲህ ያለውን ሰው ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት።
የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፤ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።
አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።
ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፤