3 ዮሐንስ 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአሕዛብ አንዳች ሳይቀበሉ ስለ ስሙ ወጥተዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ስሙ የወጡት ከአሕዛብ ምንም ሳይቀበሉ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ስሙ ብለው፥ ከአሕዛብ ምንም ሳይቀበሉ ወጥተዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ክርስቶስን ለማገልገል ሲወጡ ከአሕዛብ ምንም ርዳታ አልተቀበሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአሕዛብ አንዳች ሳይቀበሉ ስለ ስሙ ወጥተዋልና። |
በድካማችንና በሥራችን ነዳያንን እንቀበላቸው ዘንድ እንደሚገባን ይህን አስተምሬአችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለውንም የጌታችንን የኢየሱስን ቃል ዐስቡ።”
እንግዲህ ዋጋዬ ምንድን ነው? ወንጌልን ባስተምርም በሹመቴ የማገኘው ሳይኖር ወንጌልን ያለ ዋጋ እንዳስተምር ባደርግ ነው።
እከብድባችሁ ዘንድ ወደ እናንተ ካለመምጣቴ በቀር፥ ከአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያሳነስኋችሁ በምንድን ነው? ይህቺን በደሌን ይቅር በሉኝ።
ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታ እንደ ሆነ እንሰብካለን እንጂ ራሳችንን የምንሰብክ አይደለም፤ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም ብለን ራሳችንን ለእናንተ አስገዛን።
አሁንም በመከራዬ ደስ ይለኛል፤ አካሉ ስለ ሆነች ስለ ቤተ ክርስቲያን፥ ከክርስቶስ መከራ ጥቂቱን በሥጋዬ እፈጽማለሁ።