Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ቈላስይስ 1:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አሁ​ንም በመ​ከ​ራዬ ደስ ይለ​ኛል፤ አካሉ ስለ ሆነች ስለ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን፥ ከክ​ር​ስ​ቶስ መከራ ጥቂ​ቱን በሥ​ጋዬ እፈ​ጽ​ማ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ስለ እናንተ በተቀበልሁት መከራ አሁንም ደስ ይለኛል፤ ክርስቶስ ስለ አካሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን ከተቀበለው መከራ የጐደለውን በሥጋዬ አሟላለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 አሁን በመከራዬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ አካሉም ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ካለፈባቸው መከራዎች መካከል የጐደሉትን በሥጋዬ እፈጽማለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል፤ አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጐደለብኝን በሥጋዬ አሟላለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 አሁን በመከራዬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፥ ስለ አካሉም ማለት ስለ ቤተ ክርስቲያን በሥጋዬ በክርስቶስ መከራ የጐደለውን እፈጽማለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ቈላስይስ 1:24
21 Referencias Cruzadas  

የም​ን​መካ በእ​ር​ስዋ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በመ​ከ​ራ​ችን ደግሞ እን​መ​ካ​ለን እንጂ፤ መከራ በእና ላይ ትዕ​ግ​ሥ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​መጣ እና​ው​ቃ​ለ​ንና።


እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኀይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፤


በእ​ር​ሱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ የመ​ነ​ሣ​ቱ​ንም ኀይል በሕ​ማሙ እሳ​ተ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ በሞ​ቱም እመ​ስ​ለ​ዋ​ለሁ።


በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ዲሁ ብዙ መወ​ደድ አለኝ፤ ስለ እና​ን​ተም የም​መ​ካ​በት ብዙ ነው፤ መጽ​ና​ና​ት​ንም አገ​ኘሁ፤ ከመ​ከ​ራ​ዬም ሁሉ ይልቅ ደስ​ታዬ በዛ​ልኝ።


ስለ​ዚ​ህም ስለ እና​ንተ ለክ​ብ​ራ​ችሁ የም​ታ​ገ​ኘ​ኝን መከ​ራ​ዬን ቸል እን​ዳ​ይ​ላት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እማ​ል​ደ​ዋ​ለሁ።


ወንድሞቼ ሆይ! የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤


እርሱ የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስ ነው፤ በኵር እርሱ ለሁሉ ራስ ይሆን ዘንድ ከሙ​ታን ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አ​ልና።


እነ​ር​ሱም ከሸ​ን​ጎው ፊት ደስ እያ​ላ​ቸው ወጡ፤ ስለ ስሙ መከራ ይቀ​በሉ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ አድ​ሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


ስለ​ዚህ አሕ​ዛብ ሆይ ስለ እና​ንተ እኔ ጳው​ሎስ የክ​ር​ስ​ቶስ እስ​ረ​ኛው ነኝ።


ይህ​ች​ውም አካሉ ናት፤ የሁ​ሉም ፍጻ​ሜው እርሱ ነው፤ ሁሉ​ንም በሁሉ ይፈ​ጽ​ማል።


እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ከሆን ወራ​ሾቹ ነን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወራ​ሾች ከሆ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ወራ​ሾቹ ነን፤ በመ​ከራ ከመ​ሰ​ል​ነ​ውም በክ​ብር እን​መ​ስ​ለ​ዋ​ለን።


እን​ግ​ዲህ እና​ንተ የክ​ር​ስ​ቶስ አካሉ ናችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም የአ​ካሉ ክፍ​ሎች ናችሁ።


ኀዘ​ን​ተ​ኞች ስን​ሆን ዘወ​ትር ደስ​ተ​ኞች ነን፤ እንደ ድሆች ስን​ሆን ብዙ​ዎ​ችን እና​በ​ለ​ጽ​ጋ​ለን፤ ምንም የሌ​ለን ስን​ሆን ሁሉ በእ​ጃ​ችን ነው።


እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወ​ጣ​ለሁ፤ ስለ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እጅግ ብወ​ዳ​ችሁ ራሴን ወደ​ድሁ።


እነርሱም “እንችላለን፤” አሉት። ኢየሱስም “እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios