እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እርሱም በንጉሡ ዘንድ የተሾመ እንደ ሆነ አታውቁምን? እነዚህም ሰዎች የሦርህያ ልጆች በርትተውብኛል፤ እግዚአብሔርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት” አላቸው።
2 ጢሞቴዎስ 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንጥረኛው እስክንድሮስ ብዙ ጕዳት አድርሶብኛል፤ ጌታ ግን የእጁን ይሰጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ ብዙ ክፉ ነገሮችን አድርጎብኛል፤ ጌታ እንደ ሥራው ብድራቱን ይከፍለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የናስ አንጥረኛው እስክንድር ከፍተኛ ጒዳት አደረሰብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይከፍለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል። |
እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እርሱም በንጉሡ ዘንድ የተሾመ እንደ ሆነ አታውቁምን? እነዚህም ሰዎች የሦርህያ ልጆች በርትተውብኛል፤ እግዚአብሔርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመልስበት” አላቸው።
አቤቱ! አንተ ታውቃለህ፤ አስበኝ፤ ጐብኘኝም፤ ከሚያሳድዱኝም አድነኝ እንጂ፥ አትታገሣቸው፤ ስለ አንተ እንደ ሰደቡኝ አስብ።
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።
ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።
ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።
በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።
እነሆ፥ የልብስህ ዘርፍ በእጄ እንዳለ ተመልክተህ ዕወቅ፤ የልብስህንም ዘርፍ በቈረጥሁ ጊዜ አልገደልሁህም፤ ስለዚህም በእጄ ክፋት፥ በደልና ክዳት እንደሌለ፥ አንተንም እንዳልበደልሁህ ዕወቅ፤ አንተ ግን ነፍሴን ልታጠፋ ታጠምዳለህ።