2 ጢሞቴዎስ 2:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ በጎ ወታደር ከእኛ ጋራ መከራን ተቀበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ መልካም ወታደር ሆነህ መከራን ተቀበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተም የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ወታደር በመሆን ከእኔ ጋር መከራን ተቀበል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። |
የሚያገለግልም ምግቡን ያገኝ ዘንድ ነው፤ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? መንጋውንስ ጠብቆ ወተቱን የማይጠጣ ማን ነው?
መከራ ብንቀበልም እናንተ እንድትድኑና እንድትጽናኑ ነው፤ ብንጽናናም እኛ የተቀበልነውን ያን መከራ በመታገሥ ስለሚደረግ መጽናናታችሁ ነው።
እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኀይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፤
ይህም ጦርነትን ያስተምሩአቸው ዘንድ ስለ እስራኤል ልጆች ትውልድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ከእነርሱ በፊት የነበሩት እነዚህን አላወቋቸውም ነበር፤