2 ሳሙኤል 8:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ዳዊትም ለሕዝቡ ሁሉ ፍርድንና ጽድቅን አደረገላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕና ርትዕ አሰፈነላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ትክክለኛ ፍርድ አሰፈነላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ዳዊት የመላው እስራኤል ንጉሥ ሆኖ ሕዝቡ ዘወትር ትክክለኛ ፍርድ ማግኘት እንዲችል ጥረት ያደርግ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፥ ዳዊትም ለሕዝቡ ሁሉ ፍርድንና ጽድቅን አደረገላቸው። |
ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ አለቃ ነበረ፤
አበኔርም ለዳዊት፥ “ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፤ እጄም ከአንተ ጋር ትሆናለች፤ እስራኤልንም ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ” ብለው በስሙ ይነግሩት ዘንድ መልእክተኞችን ወዲያውኑ ላከለት።
በኬብሮን በይሁዳ ላይ ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም በእስራኤል ሁሉና በይሁዳ ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።
መላዋን ኤዶምያስን ይጠብቁ ዘንድ በኤዶምያስ ሁሉ ጭፍሮችን አኖረ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሚሄድበት ቦታ ሁሉ ጠበቀው።
አንተን በእስራኤል ዙፋን ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደ አምላክህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለም ያጸናው ዘንድ ወድዶታልና ስለዚህ በየነገራቸው ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ፤ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፤ ምናልባት ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።
እነርሱ በእምነት ተጋደሉ፤ ነገሥታትን ድል ነሡ፤ ጽድቅን አደረጉ፤ ተስፋቸውን አገኙ፤ የአናብስትንም አፍ ዘጉ ።
ሳኦልም መንግሥቱን በእስራኤል ላይ አጸና፤ በዙሪያውም ካሉት ከጠላቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞዓብም፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከኤዶምያስም፥ ከቢዖርም፥ ከሱባም ነገሥታት፥ ከፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየሄደበትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።