የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልእክተኞችን፥ የዝግባ እንጨትንም፥ አናጢዎችንም፥ ድንጋይ ጠራቢዎችንም ላከ፤ ለዳዊትም ቤት ሠሩለት።
2 ሳሙኤል 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳዘጋጀው፥ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤልም መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገ ዐወቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥነቱን እንዳጸናለት፣ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤልም ሲል መንግሥቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት ተገነዘበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በእስራኤል ላይ ንጉሥነቱን እንዳጸናለት፥ ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል መንግሥቱን እንዳሰፋለት ዳዊት ዐወቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም እግዚአብሔር የእስራኤል ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናውና ለሕዝቡም ሲል መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገለት ተገነዘበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናው፥ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤልም መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገ አወቀ። |
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልእክተኞችን፥ የዝግባ እንጨትንም፥ አናጢዎችንም፥ ድንጋይ ጠራቢዎችንም ላከ፤ ለዳዊትም ቤት ሠሩለት።
ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ እንደ ገና ቁባቶቹንና ሚስቶቹን ከኢየሩሳሌም ወሰደ፤ ለዳዊትም ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ተወለዱለት።
አንተን በእስራኤል ዙፋን ያስቀምጥህ ዘንድ የወደደ አምላክህ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ እግዚአብሔር እስራኤልን ለዘለዓለም ያጸናው ዘንድ ወድዶታልና ስለዚህ በየነገራቸው ጽድቅና ፍርድ ታደርግ ዘንድ በላያቸው አነገሠህ።”
ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል፥ መንግሥቱ እጅግ ከፍ ብሎአልና እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን እንዳዘጋጀው ዳዊት ዐወቀ።