በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሁለተኛው አለቃ ከጎቶንያል ወገን የነበረው ነጦፋታዊው ኬልዳይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
2 ሳሙኤል 23:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአንጢፋ ሰው የቦአና ልጅ ሔሌብ፥ ከብንያም ወገን ከጌብዓ የረባይ ልጅ ኢታይ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፣ ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፥ ከብንያም ተወላጅ የሆነው የጊብዓ ሰው የሪባይ ልጅ ኢታይ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነጦፋዊው ኖኤሬ፥ የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፥ ከብንያም ወገን ከጊብዓ የሪባይ ልጅ ኢታይ፥ |
በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሁለተኛው አለቃ ከጎቶንያል ወገን የነበረው ነጦፋታዊው ኬልዳይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃርሔም ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፥ የተንሁሜትም ልጅ ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች፥ የመከጢ ልጅ አዛንያም ከሰዎቻቸው ጋር ወደ ጎዶልያስ ወደ መሴፋ መጡ።
ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡሴዎን ከተማና የኢያሪሞን ከተማ ገባዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
ያንጊዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎችን ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱም ሺህ በማኪማስና በቤቴል ተራራ ከሳኦል ጋር ነበሩ፤ አንዱም ሺህ በብንያም ገባዖን ከልጁ ከዮናታን ጋር ነበሩ፤ የቀረውንም ሕዝብ እያንዳንዱን ወደ ድንኳኑ አሰናበተ።