እርሱ ግን ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ አቤል፥ ወደ ቤተማካም ሁሉ አለፈ፤ በካሪ ያሉ ሰዎችም ሁሉ ደግሞ ተሰብስበው ተከተሉት።
2 ሳሙኤል 20:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤተ ማካና በአቤልም መጥተው ከበቡት፤ በከተማዪቱም ላይ እስከ ቅጥርዋ ድረስ የአፈርን ድልድል ደለደሉ፤ እነርሱም ከአጥሩ ቀጥሎ ቆሙ፤ ቅጥሩንም ያፈርሱ ዘንድ ከኢዮአብ ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ተስማሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢዮአብ ጋራ ያለውም ሰራዊት መጥቶ፣ ሳቤዔን በአቤል ቤትመዓካ በኩል ከበበው፤ በስተ ውጭም እስከ ከተማዪቱ ግንብ ጫፍ ድረስ ዙሪያውን የዐፈር ድልድል ሠሩ፤ ግንቡን ለመናድ በኀይል በሚደበድቡበት ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኢዮአብ ጋር ያለውም ሠራዊት መጥቶ ሼባዕን በአቤል ቤት መዓካ በኩል ከበበው፤ በስተ ውጭም እስከ ከተማዪቱ ግንብ ጫፍ ድረስ ዙሪያውን የዐፈር ድልድል ሠሩ፤ ግንቡን ለመናድ በኃይል ይደበድቡት ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮአብ ወታደሮች ሼባዕ እዚያ መሆኑን ስለ ሰሙ ሄደው ከተማይቱን ከበቡ፤ በስተውጪ በኩል ቅጽሩን አስደግፈው የዐፈር ቊልል ሠሩ፤ ቀጥሎም ቅጽሩ እንዲወድቅ ከስሩ መቈፈር ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤትመዓካ ባለ በአቤልም መጥተው ከበቡት፥ በከተማይቱም ላይ እስከ ቅጥርዋ ድረስ የአፈርን ድልድል ደለደሉ፥ ቅጥሩንም ያፈርሱ ዘንድ ከኢዮአብ ጋር የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ይደባደቡ ነበር። |
እርሱ ግን ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ አቤል፥ ወደ ቤተማካም ሁሉ አለፈ፤ በካሪ ያሉ ሰዎችም ሁሉ ደግሞ ተሰብስበው ተከተሉት።
ወልደ አዴርም ለንጉሡ ለአሳ እሺ አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰድዶ ኢናንንና ዳንን፥ አቤልቤትመዓካንና ኬኔሬትን ሁሉ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ መታ።
በእስራኤልም ንጉሥ በፋቁሔ ዘመን የአሶር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር መጣ፤ ኢዮንና አቤልቤትመዓካን፥ ያኖዋንም፥ ቃዴስንና አሶርንም፥ ገለዓድንና ገሊላንም፥ የንፍታሌምንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶርም አፈለሳቸው።
እንደዚህ አይደለምን? እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፥ “ወደዚች ከተማ አይገባም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፤ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም ድልድል አይደለድልባትም።
ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ወደዚች ከተማ አይመጣም፤ ፍላጻንም አይወረውርባትም፤ በጋሻም አይመጣባትም፥ አያጥራትምም።
አሕዛብም መጥተው ይህችን ሀገር ያዟት፤ ይህችም ከተማ ከረኃቡና ከጦሩ የተነሣ በወጓት በከለዳውያን ሰዎች እጅ ወደቀች፤ እንደ ተናገርኸውም ሆነ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለምሽግና ለመከላከያ ስለ ፈረሱት ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና፦
ኀያል እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ ኀይልን አፍስሱ ይህች ከተማ የሐሰት ከተማ ናት፤ መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።
በውስጧም የሚዋጉበት ግንብን ሥራ፤ በሠራዊትም ክበባት፤ በዙሪያዋም ጦር አስፍር፤ የሚዋጋ ጦርንም ወደ አደባባይዋ ላክ።
ጠላቶችሽ አንቺን የሚከቡበት ቀን ይመጣል፤ ይከትሙብሻል፤ ያስጨንቁሻልም፤ በአራቱ ማዕዘንም ከብበው ይይዙሻል።