እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው፤ እርሱም ታናሽ ነበረ፤ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆቹንም አስተላለፈ።
2 ሳሙኤል 19:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ አገልጋይህ በደለኛ እንደ ሆንሁ አውቄአለሁና እነሆ፥ ከዮሴፍ ቤት ሁሉ አስቀድሜ ዛሬ መጣሁ፤ ጌታዬንም ንጉሡን ልቀበል ወረድሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ አገልጋይህ ኀጢአት መሥራቴን ዐውቃለሁና፤ ዛሬ ግን ጌታዬን ንጉሡን ለመቀበል ከዮሴፍ ቤት ሁሉ የመጀመሪያ ሆኜ እነሆ መጥቻለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ በደሌን አትቁጠርብኝ፥ ጌታዬ ንጉሡ፥ ከኢየሩሳሌም በወጣህ ቀነ አገልጋይህ የበደልሁህን አታስብብኝ፥ በልብህም አታኑርብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታዬ ሆይ! ኃጢአት እንደ ሠራሁ ዐውቃለሁ፤ ዛሬ ግን ከሰሜን የእስራኤል ነገዶች የመጀመሪያው በመሆን አንተን ለመቀበል መጥቼአለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያህ በደለኛ እንደ ሆንሁ አውቄአለሁና እነሆ፥ ከዮሴፍ ቤት ሁሉ አስቀድሜ ዛሬ መጣሁ፥ ጌታዬንም ንጉሡን ልቀበል ወረድሁ አለው። |
እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው፤ እርሱም ታናሽ ነበረ፤ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆቹንም አስተላለፈ።
በዚያም ቀን እንዲህ ብሎ ባረካቸው፥ “በእናንተ እስራኤል እንዲህ ተብሎ ይባረካል፦ እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ይባርክህ።” ኤፍሬምንም ከምናሴ ፊት አደረገው።
ንጉሡ ዳዊትም ወደ በውሪም መጣ፤ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየሄደም ይረግመው ነበር።
የሶርህያ ልጅ አቢሳ ግን፥ “ሳሚ እግዚአብሔር የቀባውን ሰድቦአልና እንግዲህ ሞት የተገባው አይደለምን?” ብሎ መለሰ።
ከመላው ነገደ እስራኤል የተሰበሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠላቶቻችን እጅ ታድጎናል፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አድኖናል፤ አሁንም ስለ አቤሴሎም ከሀገሩና ከመንግሥቱ ሸሸ።
ከዚህም በኋላ እስራኤል በሙሉ ኢዮርብዓም ከግብፅ እንደ ተመለሰ በሰሙ ጊዜ ልከው ወደ ሸንጎአቸው ጠሩት፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ አነገሡት። ከብቻው ከይሁዳና ከብንያም ነገድ በቀር የዳዊትን ቤት የተከተለ ማንም አልነበረም።
አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ የምታለቅሺ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ትጨነቂያለሽ!
እኔ ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፤ እስራኤልም ከእኔ አልራቀም፤ ኤፍሬም ዛሬ አመንዝሮአልና፤ እስራኤልም ረክሶአልና።