ዳዊትም አቢሳንና አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “እነሆ፥ ከወገቤ የወጣው ልጄ ነፍሴን ይሻል፤ ይልቁንስ ይህ የኢያሚን ልጅ እንዴት ነዋ? እግዚአብሔር አዝዞታልና ተዉት፥ ይርገመኝ።
2 ሳሙኤል 18:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ኢዮአብንና አቢሳን ኤቲንም፥ “ለብላቴናው ለአቤሴሎም ስለ እኔ ራሩለት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡም ስለ አቤሴሎም አለቆቹን ሁሉ ሲያዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ኢዮአብን፣ አቢሳንና ኢታይን፣ “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ ልጄ በአቤሴሎም ላይ ጕዳት እንዳታደርሱበት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡ ልጁን አቤሴሎምን አስመልክቶ ለእያንዳንዱ አዛዥ ትእዛዝ ሲሰጥ ሰራዊቱ ሁሉ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ኢዮአብን፥ አቢሳንና ኢታይን፥ “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ ልጄ በኤቤሴሎም ላይ ጉዳት እንዳታደርሱበት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡ ልጁን አቤሴሎምን አስመልክቶ ለአዛዥዎቹ ትእዛዝ ሲሰጥ ሕዝቡ ሁሉ ሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኢዮአብ፥ ለአቢሳና ለኢታይም “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ በአቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት” የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው፤ ዳዊት ይህን ትእዛዝ ለጦር አዛዦቹ በሰጠ ጊዜም ወታደሮቹ ሁሉ ይሰሙ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ኢዮአብንና አቢሳን ኢታይንም፦ ለብላቴናው ለአቤሴሎም ስለ እኔ ራሩለት ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡም ስለ አቤሴሎም አለቆቹን ሁሉ ሲያዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰማ። |
ዳዊትም አቢሳንና አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “እነሆ፥ ከወገቤ የወጣው ልጄ ነፍሴን ይሻል፤ ይልቁንስ ይህ የኢያሚን ልጅ እንዴት ነዋ? እግዚአብሔር አዝዞታልና ተዉት፥ ይርገመኝ።
አቤሴሎምና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ “የአርካዊው የኩሲ ምክር ከአኪጢፌል ምክር ይሻላል” አሉ። እግዚአብሔርም በአቤሴሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግዚአብሔር መልካሚቱን የአኪጦፌልን ምክር እንዲበትን አዘዘ።
ሰውየውም ኢዮአብን፥ “ንጉሡ አንተንና አቢሳን፥ ኤቲንም፦ ብላቴናውን አቤሴሎምን ጠብቁ ብሎ ሲያዝ እኛ በጆሮአችን ሰምተናልና ሺህ ሰቅል ብር በእጄ ላይ ብትመዝን እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ አልዘረጋም ነበር።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን ኣያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ፤ በልብሱም ላይ ዕጣ ተጣጣሉና ተካፈሉ።