እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራው” ተባባሉ።
2 ሳሙኤል 18:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም በሕይወቱ ሳለ፥ “ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም” ብሎ ሐውልት ወስዶ በንጉሥ ሸለቆ ውስጥ ለራሱ በስሙ አቁሞ ነበር፤ ያችም ሐውልት እስከ ዛሬ ድረስ “እደ አቤሴሎም” ተብላ ትጠራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎም፣ “ስሜን የሚያስጠራ ልጅ የለኝም” በማለት መታሰቢያ እንዲሆነው በሕይወት እያለ የንጉሥ ሸለቆ በተባለው ስፍራ በራሱ ስም ሐውልት አቁሞ ስለ ነበር፣ እስከ ዛሬ ድረስ የአቤሴሎም ሐውልት ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሴሎም፥ “ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም” በማለት መታሰቢያ እንዲሆነው በሕይወት እያለ የንጉሥ ሸለቆ በተባለው ስፍራ ለራሱ ሐውልት አቁሞ ስለ ነበር፥ እስከ ዛሬ ድረስ የአቤሴሎም ሐውልት ተብሎ ይጠራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሴሎም ስሙን የሚያስጠራለት ወንድ ልጅ አልነበረውም፤ ስለዚህም በሕይወት በነበረበት ዘመን “የንጉሥ ሸለቆ” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ለራሱ ሐውልት አሠርቶ ነበር፤ በራሱም ስም ሰይሞት ስለ ነበር እስከ ዛሬ ድረስ “የአቤሴሎም ሐውልት” እየተባለ ይጠራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም ሕያው ሳለ፦ ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም ብሎ ሐውልት ወስዶ በንጉሥ ሸለቆ ውስጥ ለራሱ አቁሞ ነበር፥ ሐውልቱንም በስሙ ጠርቶት ነበር፥ እስከ ዛሬም ድረስ የአቤሴሎም መታሰቢያ ተብሎ ይጠራል። |
እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራው” ተባባሉ።
ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፤ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቆአልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ፊት ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
ኮሎዶጎሞርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ወግቶ ከተመለሰም በኋላ የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሜዳ በሆነ በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ።
ለአቤሴሎምም ሦስት ወንዶች ልጆችና አንዲት ሴት ልጅ ተወለዱለት። የሴቲቱ ልጅም ስም ትዕማር ይባላል። ያችውም ሴት መልከ መልካም ነበረች፤ እርሷም የሰሎሞን ልጅ የሮብአም ሚስት ሆና አቢያን ወለደችለት።
መቃብር በዚያ ያስወቀርህ፥ ከፍ ባለው ስፍራ መቃብር ያሠራህ፥ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖርያ ያሳነጽህ ወደዚህ ለምን መጣህ? ለምንስ በዚህ ተደፋፈርህ?
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዘመኑ አይከናወንምና፥ ከዘሩም በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ አይነሣምና፥ እንግዲህ ወዲህም ለይሁዳ ገዢ አይሾምምና ይህን ሰው እንደ ሞተ ቍጠሪው” አለ።
ሳሙኤልም እስራኤልን ለመገናኘት በጥዋት ገሥግሦ ሄደ። ለሳሙኤልም፥ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ መጣ፤ እነሆም፥ ለራሱ የመታሰቢያ ዐምድ አቆመ” ብለው ነገሩት። ሳሙኤልም ሰረገላውን መልሶ ወደ ጌልጌላ ወደ ሳኦል ወረደ፤ ከአማሌቅ ዘንድ ከአመጣውም ከአማረው ከምርኮው መንጋ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሲሠዋ አገኘው፤