La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 17:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በተ​ራ​ራው ላይ፥ ያም ባይ​ሆን በአ​ንድ ቦታ ተሰ​ው​ሮ​አ​ልና ከእ​ነ​ርሱ ፊተ​ኞቹ ቢወ​ድቁ የሚ​ሰ​ማው ሁሉ አቤ​ሴ​ሎ​ምን የተ​ከ​ተለ ሕዝብ ተመታ ይላል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል። እርሱ ቀድሞ አደጋ በመጣል ከሰዎችህ ጥቂት ቢሞቱ ይህን የሰማ ሁሉ፣ ‘አቤሴሎምን የተከተለው ሰራዊት ዐለቀ’ ብሎ ያወራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፥ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል። ጥቂት ሰዎች በመጀመሪያ በሚጥልባቸው ጥቃት ቢሞቱ ይህን የሰማ ሁሉ፥ ‘አቤሴሎምን የተከተለው ሠራዊት ተፈጀ’ ብሎ ያወራል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምናልባት አሁን እንኳ በዋሻ ውስጥ ወይም በሌላ ስፍራ ተሸሽጎ ሊሆን ይችላል፤ ዳዊት በአንተ ሠራዊት ላይ አደጋ እንደ ጣለባቸው የሚሰማ ሰው ሁሉ ወዲያውኑ ወታደሮችህ እንደ ተሸነፉ አድርጎ ያወራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁንም ምናልባት በአንድ ጉድጓድ ወይም በማናቸውም ስፍራ ተሸሽጎ ይሆናል፥ በመጀመሪያም ከእነርሱ አያሌዎች ቢወድቁ፥ የሚሰማው ሁሉ፦ አቤሴሎምን የተከተለው ሕዝብ ተመታ ይላል።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 17:9
10 Referencias Cruzadas  

እርሱ ኀይ​ለኛ ሰው ነውና፥ ልቡም እንደ አን​በሳ ልብ ፈጽሞ ይና​ደ​ዳ​ልና፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አባ​ትህ ጽኑዕ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት ስዎች ኀያ​ላን እንደ ሆኑ ያው​ቃሉ።


ኩሲ ደግሞ አለ፥ “በሜዳ እን​ዳ​ለች አራስ ድብና እንደ ተኳር የዱር እሪያ በል​ባ​ቸው መራ​ሮ​ችና ኀያ​ላን መሆ​ና​ቸ​ውን አባ​ት​ህ​ንና ሰዎ​ቹን ታው​ቃ​ለህ፤ አባ​ትህ አር​በኛ ነው፤ ሕዝ​ቡ​ንም አያ​ሰ​ና​ብ​ትም።


እስ​ማ​ኤ​ልም ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን ሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣ​ለ​በት ጕድ​ጓድ ንጉሡ አሳ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ባኦ​ስን ስለ ፈራ የሠ​ራው ጕድ​ጓድ ነበረ፤ የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን ሞላ​በት።


የጋይ ሰዎ​ችም ከእ​ነ​ርሱ ሠላሳ ስድ​ስት ሰዎ​ችን ገደሉ፤ ከበሩ ጀም​ረው እስከ አጠ​ፉ​አ​ቸው ድረስ አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው፤ በቍ​ል​ቍ​ለ​ቱም ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የሕ​ዝ​ቡም ልብ ደነ​ገጠ፤ እንደ ውኃም ሆነ።


ወጥ​ተ​ውም በተ​ከ​ተ​ሉን ጊዜ ከከ​ተማ እና​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ በፊቱ ከፊ​ታ​ችን ሸሹ ይላሉ፤ እኛም ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን።


ዳዊ​ትም ከዚያ ተነ​ሥቶ አመ​ለጠ፤ ወደ ዔዶ​ላም ዋሻም መጣ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹና የአ​ባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ወደ​ዚያ ወረዱ።


አሁ​ንም ደግሞ ሂዱና አዘ​ጋጁ፤ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ት​ንም፥ ያለ​በ​ት​ንም ቦታ ሁሉ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ላ​ችሁ ፈጥ​ና​ችሁ ዕወቁ።


ሳኦ​ልም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹ​ንም ለመ​ፈ​ለግ ዋሊ​ያ​ዎች ወደ​ሚ​ታ​ደ​ኑ​ባ​ቸው ዓለ​ቶች ሄደ።