ንጉሡም ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን፥ “እነሆ፥ አንተና ልጅህ አኪማኦስ፥ የአብያታርም ልጅ ዮናታን፥ ሁለቱ ልጆቻችሁ ከእናንተ ጋር በሰላም ወደ ከተማ ተመለሱ።
2 ሳሙኤል 17:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንና አኪማሆስም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ቆመው ሳለ አንዲት ብላቴና ሄዳ ነገረቻቸው፤ ወደ ከተማ መግባት አልተቻላቸውም ነበርና፤ እነርሱም ሄደው ለንጉሡ ለዳዊት ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ዮናታንና አኪማአስ ወደ ከተማዪቱ ከገቡ ስለሚታዩ በዓይንሮጌል ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይ ወደዚያ እየሄደች በምትነግራቸው ጊዜ፣ እነርሱ ደግሞ ይህንኑ ወስደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ዮናታንና አሒማዓጽ ወደ ከተማዪቱ ከገቡ ስለሚታዩ በዔንሮጌል ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይ ወደዚያ እየሄደች በምትነግራቸው ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ ይህንኑ ወስደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአብያታር ልጅ ዮናታንና የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ወደ ከተማይቱ ሲገቡ ማንም እንዳያያቸው ስለ ፈሩ፥ ከኢየሩሳሌም አካባቢ ባለችው በዔንሮጌል ምንጭ አጠገብ ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይም ዘወትር ወደዚያ እየሄደች የሚሆነውን ነገር ሁሉ ትነግራቸው ነበር፤ ከዚያም በኋላ እነርሱ ሄደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንና አኪማአስ ተገልጠው ወደ ከተማ ይገቡ ዘንድ አልቻሉም ነበርና በዓይንሮጌል ተቀምጠው ነበር፥ አንዲትም ባሪያ ሄዳ ትነግራቸው ነበር፥ እነርሱም ሄደው ለንጉሡ ለዳዊት ይነግሩት ነበር። |
ንጉሡም ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን፥ “እነሆ፥ አንተና ልጅህ አኪማኦስ፥ የአብያታርም ልጅ ዮናታን፥ ሁለቱ ልጆቻችሁ ከእናንተ ጋር በሰላም ወደ ከተማ ተመለሱ።
እነሆ፥ ካህናቱ ሳዶቅና አብያታርም በዚያ ከአንተ ጋር ናቸው። ከንጉሡ ቤትም የምትሰማውን ነገር ሁሉ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ንገራቸው።
እነሆ፥ የሳዶቅ ልጅ አኪማኦስና የአብያታር ልጅ ዮናታን፥ ልጆቻቸው በዚያ ከእነርሱ ጋር አሉ፤ የምትሰሙትን ሁሉ በእነርሱ እጅ ላኩልኝ።”
እርሱም ይህን ሲናገር የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ፤ አዶንያስም፥ “አንተ ኀያል ሰው ነህና፥ መልካምም ታወራልናለህና ግባ” አለው።
አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን፥ ጠቦቶችንም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ባለችው በዞሔሌት ድንጋይ ዘንድ ሠዋ፤ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ የንጉሡንም አገልጋዮች፥ የይሁዳንም ኀያላን ሁሉ ጠራ።
ድንበሩም በአኮር ሸለቆ አራተኛ ክፍል ላይ ይወጣል፤ በአዱሚን ዐቀበት ፊት ለፊት፥ በደቡብ በኩል ወዳለችው ወደ ጌልገላ ይወርዳል፤ ድንበሩም ወደ ፀሐይ ምንጭ ውኃ ያልፋል፤ መውጫውም በሮጌል ምንጭ አጠገብ ነበረ፤
ድንበሩም በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፤ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ሮጌል ምንጭም ወረደ።