Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 1:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 እር​ሱም ይህን ሲና​ገር የካ​ህኑ የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ ዮና​ታን መጣ፤ አዶ​ን​ያ​ስም፥ “አንተ ኀያል ሰው ነህና፥ መል​ካ​ምም ታወ​ራ​ል​ና​ለ​ህና ግባ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ኢዮአብ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ፣ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ደረሰ፤ አዶንያስም፣ “እንደ አንተ ያለ ታማኝ ሰው መልካም ዜና ሳይዝ አይመጣምና ግባ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 እርሱም ይህን ሲናገር የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ፥ አዶንያስም፦ “አንተ መልካም ሰው ነህና፥ መልካም ታወራልናለህና ግባ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 እርሱ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን ድንገት ደረሰ፤ አዶንያስም “እስቲ ና ግባ፤ አንተ ጥሩ ሰው ስለ ሆንክ መልካም ዜና ይዘህ ሳትመጣ አትቀርም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 እርሱም ይህን ሲናገር የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ፤ አዶንያስም “አንተ መልካም ሰው ነህና፥ መልካም ታወራልናለህና ግባ፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 1:42
10 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም ደግሞ ካህ​ኑን ሳዶ​ቅን፥ “እነሆ፥ አን​ተና ልጅህ አኪ​ማ​ኦስ፥ የአ​ብ​ያ​ታ​ርም ልጅ ዮና​ታን፥ ሁለቱ ልጆ​ቻ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር በሰ​ላም ወደ ከተማ ተመ​ለሱ።


እነሆ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ኦ​ስና የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ ዮና​ታን፥ ልጆ​ቻ​ቸው በዚያ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አሉ፤ የም​ት​ሰ​ሙ​ትን ሁሉ በእ​ነ​ርሱ እጅ ላኩ​ልኝ።”


ዮና​ታ​ንና አኪ​ማ​ሆ​ስም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ቆመው ሳለ አን​ዲት ብላ​ቴና ሄዳ ነገ​ረ​ቻ​ቸው፤ ወደ ከተማ መግ​ባት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ርና፤ እነ​ር​ሱም ሄደው ለን​ጉሡ ለዳ​ዊት ነገ​ሩት።


ዘበ​ኛ​ውም፥ “የፊ​ተ​ኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪ​ማ​ሖስ ሩጫ ይመ​ስ​ላል” አለ፤ “ንጉ​ሡም፦ እርሱ መል​ካም ሰው ነው፤ መል​ካ​ምም ወሬ ያመ​ጣል” አለ።


አዶ​ን​ያ​ስና እር​ሱም የጠ​ራ​ቸው ሁሉ መብ​ሉና መጠጡ ተፈ​ጽሞ ሳለ ሰሙ፤ ኢዮ​አ​ብም የመ​ለ​ከት ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “ይህ በከ​ተማ የም​ሰ​ማው ድምፅ ምን​ድን ነው?” አለ።


ዮና​ታ​ንም ለአ​ዶ​ን​ያስ እን​ዲህ ብሎ መለሰ፥ “በእ​ው​ነት ጌታ​ችን ንጉሥ ዳዊት ሰሎ​ሞ​ንን አነ​ገ​ሠው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥን፥ “ክፉ እንጂ መል​ካም እን​ደ​ማ​ይ​ና​ገ​ር​ልኝ አላ​ል​ሁ​ምን?” አለው።


ኢዮ​ራ​ምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ፥ ሰላም ነውን?” አለ። እር​ሱም፥ “የእ​ና​ትህ የኤ​ል​ዛ​ቤል ግል​ሙ​ት​ና​ዋና መተቷ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ።


ለኃ​ጥ​አን ደስታ የላ​ቸ​ውም” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos