La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 17:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱ​ንም ወደ​ም​ና​ገ​ኝ​በት ወደ አንድ ስፍራ እን​ደ​ር​ስ​በ​ታ​ለን፤ ጠልም በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ድቅ እን​ወ​ር​ድ​በ​ታ​ለን፤ እር​ሱ​ንና ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉ ሰዎ​ችን ሁሉ አንድ ስንኳ አና​ስ​ቀ​ርም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም እርሱ የገባበት ቦታ ሁሉ ገብተን አደጋ እንጥልበታለን፤ ጤዛ በመሬት ላይ እንደሚወርድ እንወርድበታለን፤ እርሱም ሆነ ሰዎቹ አንድ እንኳ አይተርፉም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም እርሱ ይገኝበታል የተባለው ቦታ ገብተን እናገኝዋለን፥ ጠል መሬት ላይ እንደሚወርድ እንወርድበታለን፤ እርሱም ሆነ ሰዎቹ አንድ እንኳ አይተርፉም፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የትም ስፍራ ቢደበቅ ዳዊትን ፈልገን እናገኘዋለን፤ በረዶ በምድር ላይ እንደሚወርድ እንወርድበታለን፤ እርሱም ሆነ ከተከታዮቹ አንድ ሰው እንኳ በሕይወት የሚተርፍ አይኖርም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱንም ወደምናገኝበት ወደ አንድ ስፍራ እንደርስበታለን፥ ጠልም በምድር ላይ እንደሚወድቅ እንወርድበታለን፥ እርሱና ከእርሱም ጋር ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ስንኳ አናስቀርም።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 17:12
8 Referencias Cruzadas  

ሁለት የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም በፊቱ አስ​ቀ​ም​ጡና፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሡን ሰድ​ቦ​አል ብለው ይመ​ስ​ክ​ሩ​በት፤ አው​ጥ​ታ​ች​ሁም እስ​ኪ​ሞት ድረስ በድ​ን​ጋይ መት​ታ​ችሁ ግደ​ሉት።”


አሁ​ንም እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተወ​ራ​ረድ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ዕረ​ፍት አደ​ረ​ግሁ፤ የባ​ዕድ ውኃ​ንም ጠጣሁ፥ የተ​ገ​ደ​በ​ው​ንም ውኃ ሁሉ በእ​ግሬ ጫማ አደ​ር​ቃ​ለሁ።


ሥራው ምስ​ጋ​ናና የጌ​ት​ነት ክብር ነው። ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።


በተ​ሰ​ነ​ጠ​ቀም ዓለት ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር- ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም ከፍ ከፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በል​ቡም፦ ወደ ምድር የሚ​ያ​ወ​ር​ደኝ ማን ነው? እን​ደ​ሚል፥ የል​ብህ ትዕ​ቢት እጅግ አኵ​ር​ቶ​ሃል።


የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።


እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከአ​ያ​ችሁ በኋላ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያ​ችም ምድር ካለ በይ​ሁዳ አእ​ላፍ ሁሉ እፈ​ት​ሻ​ታ​ለሁ።”