አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
2 ሳሙኤል 15:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም፥ “አቤቱ የአኪጦፌልን ምክር ለውጥ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ፣ “ከአቤሴሎም ጋራ ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ብሎ ጸለየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ፥ “ከአቤሴሎም ጋር ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ “ጌታ ሆይ! እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ሲል ጸለየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት፥ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በዐመፅ መተባበሩን በሰማ ጊዜ “እግዚአብሔር ሆይ! የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት እንድትለውጥበት እለምንሃለሁ!” ሲል ጸለየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳዊት ነገሩት፥ ዳዊትም፦ አቤቱ፥ የአኪጦፌልን ምክር ስንፍና አድርገህ እንድትለውጥ እለምንሃለሁ አለ። |
አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
በእነዚያ በመጀመሪያ ወራት የመከራት የአኪጦፌል ምክር የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መጠየቅ ነበረች፤ የአኪጦፌልም ምክር ሁሉ ከዳዊትና ከአቤሴሎም ጋር እንዲሁ ነበረች።
አቤሴሎምና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ “የአርካዊው የኩሲ ምክር ከአኪጢፌል ምክር ይሻላል” አሉ። እግዚአብሔርም በአቤሴሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግዚአብሔር መልካሚቱን የአኪጦፌልን ምክር እንዲበትን አዘዘ።
አኪጦፌልም ምክሩ እንዳልሠራ ባየ ጊዜ አህያውን ጫነ፤ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አደራጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ አምላኬ ነህ፤ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን ተውኸኝ? ለምንስ አዝኜ እመለሳለሁ?” ጠላቶቼ ሁሉ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ።
የግብፅም መንፈስ በውስጣቸው ትደነግጣለች፤ ምክራቸውን አጠፋለሁ፤ እነርሱም አማልክቶቻቸውንና ጣዖቶቻቸውን፥ ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ይጠይቃሉ።
በሟርት ሙት እናስነሣለን የሚሉትን፥ ከልባቸውም አንቅተው ሐሰት የሚናገሩትን ሰዎች ምልክት የሚለውጥ ማን ነው? ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ ይመልሳል፤ ምክራቸውንም ስንፍና ያደርጋል።
ነገር ግን ይህን የምናገር ስለ ሁላችሁ አይደለም፤ የመረጥኋቸው እነማን እንደ ሆኑ እኔ አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ‘እንጀራዬን የሚመገብ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።
እንግዲህ ጥበበኛ ማን ነው? ጸሓፊስ ማን ነው? ይህን ዓለምስ የሚመረምረው ማን ነው? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ስንፍና አላደረገውምን?