2 ሳሙኤል 15:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት ወጣ፤ ሲወጣም ያለቅስ ነበር፤ ራሱንም ተከናንቦ ነበር፤ ያለጫማም ይሄድ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተከናንበው ነበር፤ እያለቀሱም ይወጡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ግን እያለቀሰ የደብረ ዘይትን ተራራ ሽቅብ ወጣ፤ ራሱን ተከናንቦ፣ ባዶ እግሩን ነበር፤ ዐብሮት ያለውም ሕዝብ ሁሉ እንደዚሁ ራሱን ተከናንቦ እያለቀሰ ሽቅብ ይወጣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ግን እያለቀሰ፥ ራሱን ተከናንቦ፥ ባዶ እግሩን የደብረ ዘይትን ተራራ ወጣ፤ አብሮት ያለውም ሕዝብ ሁሉ እንደዚሁ ራሱን ተከናንቦ እያለቀሰ ተራራውን ይወጣ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ሐዘኑን በመግለጥ ጫማ ሳያደርግ ራሱን ተከናንቦ የደብረ ዘይትን አቀበት እያለቀሰ ወጣ፤ የተከተሉትም ሁሉ ደግሞ ራሳቸውን ተከናንበው ያለቅሱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ተከናንቦ ያለ ጫማ እያለቀሰ ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት ወጣ፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተከናንበው እያለቀሱ ወጡ። |
ኢዮአብም ወደ ንጉሡ ወደ ቤት ገብቶ እንዲህ አለ፥ “ዛሬ ነፍስህንና የወንዶችንና የሴቶች ልጆችህን ነፍስ፥ የሚስቶችህንና የቁባቶችህን ነፍስ ያዳኑትን የአገልጋዮችህን ሁሉ ፊት በዚች ቀን አሳፍረሃል።
በቀስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙታንን ልቅሶ አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፤ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ ከንፈሮችህንም አትሸፍን፤ የዕዝን እንጀራንም አትብላ።”
መጠምጠሚያችሁም በራሳችሁ፥ ጫማችሁም በእግራችሁ ይሆናል፤ ዋይ አትሉም፤ አታለቅሱምም፤ በኀጢአታችሁም ትሰለስላላችሁ፤ ሁላችሁም ጓደኞቻችሁን ታጽናናላችሁ።
በዚያም ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ፣ ደብረ ዘይትም በመካከል ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል፣ የተራራውም እኵሌታ ወደ ሰሜን፥ እኵሌታውም ወደ ደቡብ ይርቃል።
ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት መውረጃም በደረሱ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ በሙሉ ስለ አዩት ኀይል ሁሉ ደስ ይላቸውና እግዚአብሔርን በታላቅ ቃል ያመሰግኑት ዘንድ ጀመሩ።
ከዚህም በኋላ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ እርሱም ለኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው።
አንዱ የአካል ክፍል ቢታመም ከእርሱ ጋር የአካል ክፍሎች ሁሉ ይታመማሉ፤ አንዱ የአካል ክፍል ደስ ቢለውም የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።