La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤ​ሴ​ሎ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ በበሩ ጎዳና ይቆም ነበር፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ከን​ጉሥ ለማ​ስ​ፈ​ረድ ጉዳይ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ወደ እርሱ እየ​ጠራ፥ “አንተ ከወ​ዴት ከተማ ነህ?” ብሎ ይጠ​ይቅ ነበር። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ከአ​ን​ዲቱ ነኝ” ይለው ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ሆነ ብሎ ይቆም ነበር። ማንኛውም ባለጕዳይ አቤቱታውን ለንጉሡ አቅርቦ ለማስወሰን በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ፣ አቤሴሎም ወደ እርሱ እየጠራ፣ “አንተ ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው?” በማለት ይጠይቀዋል፤ ያም ሰው፣ “አገልጋይህ ከአንዱ የእስራኤል ነገዶች ነው” ብሎ ይመልስለታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማዪቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆም ነበር። ማናቸውም ባለ ጉዳይ አቤቱታውን ለንጉሡ አቅርቦ ለማስወሰን በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ፥ አቤሴሎም ወደ እርሱ እየጠራ፥ “አንተ ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው?” በማለት ይጠይቀዋል፤ ያም ሰው፥ “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች ከአንዱ ነው” ብሎ ይመልስለታል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በማለዳ እየተነሣ በመሄድ ወደ ከተማይቱ ቅጽር በር በሚያስገባው መንገድ ዳር ይቆም ነበር፤ ንጉሡ ጉዳዩን እንዲያይለት የሚፈልግ ጠብ ክርክር ያለበት ሰው ሁሉ ወደዚያ ሲመጣ አቤሴሎም ጠርቶ ከወዴት እንደ መጣ ይጠይቀዋል፤ ሰውየው ከየትኛው ነገድ መሆኑን ከነገረው በኋላ፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ በበሩ አደበባይ ይቆም ነበር፥ አቤሴሎምም ከንጉሥ ለማስፈረድ ጉዳይ የነበረውን ሁሉ ወደ እርሱ እየጠራ፦ አንተ ከወዴት ከተማ ነህ? ብሎ ይጠይቅ ነበር። እርሱም፦ እኔ ባሪያህ ከእስራኤል ነገድ ከአንዲቱ ነኝ ብሎ ይመልስ ነበር።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 15:2
13 Referencias Cruzadas  

ኤሞ​ርና ልጁ ሴኬ​ምም ሄዱና ወደ ከተ​ማ​ቸው በር ደረሱ፤ ለከ​ተ​ማ​ቸ​ውም ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ብለው ነገሩ፦


ንጉ​ሡም ተነ​ሥቶ በበሩ ተቀ​መጠ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ንጉሡ በበሩ ተቀ​ም​ጧል ብለው ተና​ገሩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በበሩ ወደ ንጉሡ ፊት ወጡ። እስ​ራ​ኤ​ልም እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ድን​ኳኑ ሸሽቶ ገብቶ ነበር።


እነ​ር​ሱም፥ “በዚች ዕለት ለዚህ ሕዝብ ቸር​ነት ብታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው፥ ደስም ብታ​ሰ​ኛ​ቸው፥ መል​ካም ነገ​ር​ንም ብት​ና​ገ​ራ​ቸው፥ ሁል​ጊዜ አገ​ል​ጋ​ዮች ይሆ​ኑ​ል​ሃል” ብለው ተና​ገ​ሩት።


ሥራ​ቸ​ው​ንም ዐውቆ ለጨ​ለማ ዳረ​ጋ​ቸው። በሌ​ሊ​ትም እንደ ሌባ ናቸው።


ዮቶ​ርም ሙሴ በሕ​ዝቡ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሁሉ አይቶ እን​ዲህ አለው፥ “ብቻ​ህን ተቀ​ም​ጠህ በሕ​ዝቡ የም​ታ​ደ​ር​ገው ይህ ምን​ድን ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥ​ዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙ​ሪ​ያህ ቆመ​ዋል።”


ነገ​ርም ቢኖ​ራ​ቸው ወደ እኔ ይመ​ጣሉ፤ በዚ​ህና በዚያ ሰውም መካ​ከል እፈ​ር​ዳ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ትና ሕግ አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው።


በሕ​ዝ​ቡም ላይ ሁል​ጊዜ ፈረዱ፤ የከ​በ​ዳ​ቸ​ው​ንም ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፤ ቀላ​ሉን ነገር ሁሉ ግን እነ​ርሱ ፈረዱ።


ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ከዐይናቸው እንቅልፋቸው ይወገዳል አይተኙምም።


ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤


“በደ​ምና በደም መካ​ከል፥ በፍ​ር​ድና በፍ​ርድ መካ​ከል፥ በመ​ቍ​ሰ​ልና በመ​ቍ​ሰል መካ​ከል፥ በክ​ር​ክ​ርና በክ​ር​ክር መካ​ከል በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ሰዎች ስለ​ሚ​ከ​ራ​ከ​ሩ​በት ክር​ክር የሚ​ሳ​ንህ የፍ​ርድ ነገር ቢኖር፥ አንተ ተነ​ሥ​ተህ ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መረ​ጠው ስፍራ ትወ​ጣ​ለህ፤


ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ፦ አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።