Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 19:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ንጉ​ሡም ተነ​ሥቶ በበሩ ተቀ​መጠ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ንጉሡ በበሩ ተቀ​ም​ጧል ብለው ተና​ገሩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በበሩ ወደ ንጉሡ ፊት ወጡ። እስ​ራ​ኤ​ልም እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ድን​ኳኑ ሸሽቶ ገብቶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህ ንጉሡ ተነሥቶ በበሩ አጠገብ ተቀመጠ፤ ለሕዝቡም፣ “እነሆ ንጉሡ በበሩ አጠገብ ተቀምጧል” ተብሎ በተነገረ ጊዜ ሕዝቡ በሙሉ ወደ ንጉሡ መጣ። በዚያ ጊዜ እስራኤላውያን በሙሉ ወደ የቤታቸው ሸሽተው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በል አሁን ተነሥተህ ውጣና አገልጋዮችህን አበረታታ፤ ባትወጣ ግን በዚች ሌሊት አንድም ሰው አብሮህ እንደማይሆን በጌታ ስም እምላለሁ፤ ይህ ደግሞ ከልጅነትህ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከደረሰብህ ክፉ ነገር ሁሉ የባሰ መከራ ያሰከትልብሃል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ በኋላ ንጉሡ ከተቀመጠበት ተነሥቶ በመሄድ በከተማይቱ ቅጽር በር አጠገብ ተቀመጠ፤ ተከታዮቹም እዚያ መሆኑን ሰምተው ሁሉም በዙሪያው ተሰበሰቡ። በዚህን ጊዜ እስራኤላውያን ሁሉ ሸሽተው እያንዳንዱ ወደየቤቱ ሄዶ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ንጉሡም ተነሥቶ በበሩ ተቀመጠ፥ ሕዝቡም ሁሉ ንጉሡ በበሩ እንደተቀመጠ ሰማ፥ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ንጉሡ ፊት መጣ።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 19:8
10 Referencias Cruzadas  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ በበሩ ጎዳና ይቆም ነበር፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ከን​ጉሥ ለማ​ስ​ፈ​ረድ ጉዳይ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ወደ እርሱ እየ​ጠራ፥ “አንተ ከወ​ዴት ከተማ ነህ?” ብሎ ይጠ​ይቅ ነበር። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ከአ​ን​ዲቱ ነኝ” ይለው ነበር።


አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ወስዶ በበ​ረሓ ባለ በታ​ላቅ ገደል ውስጥ ጣለው፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ረ​በት፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሸሽ​ተው ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ገቡ።


ዳዊ​ትም በሁ​ለት በር መካ​ከል ተቀ​ምጦ ነበር፤ ዘበ​ኛ​ውም በቅ​ጥሩ ላይ ወዳ​ለው ወደ በሩ ሰገ​ነት ወጣ፤ ዐይ​ኑ​ንም አቅ​ንቶ ብቻ​ውን የሚ​ሮጥ ሰው አየ።


ንጉ​ሡም፥ “በፊ​ታ​ችሁ መል​ካም የሚ​መ​ስ​ላ​ች​ሁን አደ​ር​ጋ​ለሁ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም በበሩ አጠ​ገብ ቆመ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መቶ በመቶ፥ ሺህ በሺህ እየ​ሆኑ ወጡ።


ከሰ​ልፍ በሸሸ ጊዜ ያፈረ ሕዝብ ተሰ​ርቆ እን​ደ​ሚ​ገባ በዚያ ቀን ሕዝቡ ተሰ​ር​ቀው ወደ ከተማ ገቡ።


ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ አዋጅ ነጋ​ሪው ወጥቶ፥ “ንጉሡ ሞቶ​አ​ልና እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ከተ​ማው፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ሀገሩ ይሂድ” ብሎ አዋጅ ነገረ።


ይሁ​ዳም በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ተመታ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ድን​ኳኑ ሸሸ።


ኢዮ​ራ​ምም ከሰ​ረ​ገ​ሎቹ ሁሉ ጋር ወደ ሲሆር አለፈ፤ ተነ​ሥ​ቶም እር​ሱ​ንና የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችን አለ​ቆች ከብ​በው የነ​በ​ሩ​ትን የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ሰዎች አጠ​ፋ​ቸው፤ ሕዝቡ ግን ወደ እየ​ቤቱ ሸሸ።


ከዚ​ህም በኋላ ተዋ​ጉ​አ​ቸው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ወደቁ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ሸሹ፤ እጅ​ግም ታላቅ ግድያ ሆነ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠላሳ ሺህ እግ​ረ​ኞች ወደቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos