2 ሳሙኤል 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም አለችው፥ “ወንድሜ ሆይ፥ አታዋርደኝ፤ እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ዘንድ አይገባምና ይህን ነውረኛ ሥራ አታድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም እንዲህ አለችው፤ “እባክህ ወንድሜ ተው አይሆንም! አታስገድደኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር በእስራኤል ተደርጎ አያውቅም፤ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አታድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም እንዲህ አለችው፤ “አይሆንም፥ ወንድሜ፥ ተው አታስገድደኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር በእስራኤል ተደርጎ አያውቅም፤ ይህን አስነዋሪ ድርጊት አትፈጽም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “አይሆንም ወንድሜ ሆይ! እባክህ አታዋርደኝ! የዚህ ዐይነቱ አሳፋሪ ተግባር በእስራኤል ተፈጽሞ አያውቅም! ስለዚህ ይህን ትልቅ ብልግና አትፈጽም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋ መልሳ፦ ወንድሜ ሆይ፥ አይሆንም፥ እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ዘንድ አይገባምና አታሳፍረኝ፥ ይህንም ነውረኛ ሥራ አታድርግ። |
የያዕቆብም ልጆች ከምድረ በዳ መጡ፤ ይህንም በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ደነገጡ፤ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፤ እጅግም ተቈጡ፤ እንዲህ አይደረግምና።
በእስራኤል ዘንድ ክፉ አድርገዋልና፥ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፥ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና። እኔም አውቃለሁ፤ ምስክርም ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
ከአባትህ የተወለደችውን የአባትህን ሚስት ልጅ ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ከአባትህ የተወለደች እኅትህ ናት፤ ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።
የእኅትህን ኀፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ በቤት ወይም በውጭ የተወለደች ብትሆን፥ ኀፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።
“ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኀፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ እርስዋም ኀፍረተ ሥጋውን ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕዝባቸውም ልጆች ፊት ይገደሉ፤ የእኅቱን ኀፍረተ ሥጋ ገልጦአልና ኀጢአቱን ይሸከማል።
ብላቴናዪቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያውጡአት፤ በእስራኤልም ዘንድ ስንፍናን አድርጋለችና፥ የአባቷንም ቤት አስነውራለችና የከተማው ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
ያ የደፈራት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናዪቱ አባት ይስጥ፤ አስነውሮአታልና ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።
ባለቤቱም ሽማግሌው ወደ እነርሱ ወጥቶ፥ “ወንድሞቼ ሆይ! ይህን ክፉ ነገር ታደርጉ ዘንድ አይገባችሁም፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ከገባ በኋላ እንደዚህ ያለ ስንፍና አትሥሩ።
እኔም ዕቅብቴን ይዤ በመለያያዋ ቈራረጥኋት፤ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ስንፍና ስለ ሠሩ ወደ እስራኤል ርስት አውራጃ ሁሉ ሰደድሁ።