ዳዊትም ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርስዋም ገባ፤ ከእርስዋም ጋር ተኛ፤ ፀነሰችም፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ሰሎሞን ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ወደደው።
2 ሳሙኤል 12:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም በነቢዩ በናታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግዚአብሔር ፍቁረ እግዚአብሔር ብሎ ጠራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሕፃኑን ስለ ወደደውም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሕፃኑን ስለ ወደደም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይዲድያ” የሚል ስም እንዲያወጣለት ነቢዩ ናታንን አዘዘው፤ ይህም “በእግዚአብሔር የተወደደ” ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በነቢዩ በናታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግዚአብሔር ይዲድያ ብሎ ጠራው። |
ዳዊትም ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርስዋም ገባ፤ ከእርስዋም ጋር ተኛ፤ ፀነሰችም፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ሰሎሞን ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ወደደው።
ናታንም የሰሎሞንን እናት ቤርሳቤህን እንዲህ ብሎ ተናገራት፥ “ጌታችን ዳዊት ሳያውቅ የአጊት ልጅ አዶንያስ እንደ ነገሠ አልሰማሽምን?
ለንጉሡም፥ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥቶአል” ብለው ነገሩት፤ እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግንባሩ በምድር ላይ ተደፍቶ ለንጉሡ እጅ ነሣ።
ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅና የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነቢዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳዊትም ኀያላን አዶንያስን አልተከተሉም ነበር።
እነሆ፥ ልጅ ይወለድልሃል፤ የዕረፍት ሰውም ይሆናል፤ በዙሪያውም ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፥ በዘመኑም ሰላምንና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ።
የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በዚህ ነገር ኀጢአት አድርጎ የለምን? በብዙ አሕዛብም መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፤ በአምላኩም ዘንድ የተወደደ ነበረ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ሁሉ ላይ አንግሦት ነበር፤ እርሱንም እንኳ እንግዶች ሴቶች አሳቱት።
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።
ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱ ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በዘመኑ ሁሉ ይጋርደዋል፤ በትከሻውም መካከል ያድራል።