እነሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ መጥቶ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እንግዲህ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ” አለው።
2 ነገሥት 9:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእውነት የናቡቴንና የልጆቹን ደም ትናንትና አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚህም እርሻ እበቀለዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ቃል ወስደህ በእርሻው ውስጥ ጣለው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ትናንት የናቡቴንና የልጆቹን ደም አይቻለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር’ ይህንም በዚሁ ዕርሻ ላይ በርግጥ አንተው እንድትከፍል አደርግሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ አሁንም በእግዚአብሔር ቃል በተነገረው መሠረት አንሣውና በዚሁ ዕርሻ ውስጥ ጣለው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ’ የሚል ነበር።” ስለዚህ ኢዩ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው” ሲል የቅርብ ረዳቱን አዘዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ’ የሚል ነበር።” ስለዚህ ኢዩ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው” ሲል የቅርብ ረዳቱን አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ‘በእውነት የናቡቴንና የልጆቹን ደም ትናንትና አይቻለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በዚህም እርሻ እመልስብሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ቃል ወስደህ በእርሻው ውስጥ ጣለው።” |
እነሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ መጥቶ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እንግዲህ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ” አለው።
ኢዮራምም፥ “ሰረገላ አዘጋጁ” አለ፤ ሰረገላውንም አዘጋጁለት። የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ሁለቱም በሰረገሎቻቸው ተቀምጠው ወጡ፤ ኢዩንም ሊገናኙት ሄዱ፤ በኢይዝራኤላዊውም በናቡቴ እርሻ ውስጥ አገኙት።
ኢዩም ጋሻጃግሬውን ቢድቃርን እንዲህ አለው፥ “አንሥተህ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ እርሻ ጣለው፤ አንተና እኔ ጎን ለጎን በፈረስ ተቀምጠን አባቱን አክዓብን በተከተልን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ይህን መከራ እንደ ተናገረበት እኔ አስባለሁና አንተም ታውቃለህና፤
ከእርሱም ዘንድ አልፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪያዎቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮአዳ ልጅ ደም ተበቅለው በአልጋው ላይ ገደሉት፤ ሞተም፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት፤ ነገር ግን በነገሥታት መቃብር አልቀበሩትም።
እንደ እግዚአብሔር ሕግ ቃል ኪዳን እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም፥ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆቻቸው፥ ልጆችም በአባቶቻቸው ፋንታ አይሙቱ” ብሎ እንዳዘዘ ልጆቻቸውን ግን አልገደለም።
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
“እናንተ ግን፦ ልጅ የአባቱን ኀጢአት ስለ ምን አይሸከምም? ትላላችሁ። ልጅ ፍርድንና ቅን ነገርን በአደረገ፥ ትእዛዜንም ሁሉ በጠበቀና በአደረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል።
“አባቶች ስለ ልጆቻቸው አይገደሉ፤ ልጆችም ስለ አባቶቻቸው አይገደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኀጢአቱ ይገደል።
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤