ሰላይም ያያቸው ዘንድ በኢይዝራኤል ግንብ ላይ ቆመ፤ ሲመጡም የእነኢዩን አቧራ አየ። “እነሆም፥ አቧራ አያለሁ” አለ። ኢዮራምም፥ “ይገናኛቸው ዘንድ አንድ ፈረሰኛ ይሂድ፤ እርሱም፦ ሰላም ነውን? ይበላቸው” አለ።
2 ነገሥት 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈረሰኛውም ሊቀበላቸው ሄዶ፥ “ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ ሰላም ነውን?” አላቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመልሰህ ተከተለኝ” አለ። ሰላዩም፥ “መልእክተኛው ደረሰባቸው፥ ነገር ግን አልተመለሰም” ብሎ ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈረሰኛውም ኢዩን ለመገናኘት ጋልቦ ሄደና፣ “ንጉሡ፣ ‘የመጣችሁት በሰላም ነውን?’ ብሏል” አለው። ኢዩም፣ “ስለ ሰላም መጨነቅ የአንተ ጕዳይ አይደለም! ይልቅስ ወደ ኋላ ዕለፍና ተከተለኝ” አለው። ጠባቂውም፣ “መልእክተኛው ከእነርሱ ዘንድ ደርሷል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ብሎ አሳወቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልእክተኛውም ጋልቦ ሄዶ ኢዩን “ንጉሡ አመጣጥህ በወዳጅነት እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋል” ሲል ጠየቀው። ኢዩም “አንተ ከሰላም ጋር ምን ግንኙነት አለህ? ይልቅስ ወደ ኋላ አልፈህ ተከተለኝ!” ሲል መለሰለት። በከተማይቱም መጠበቂያ ግንብ ላይ የነበረው ዘብ “መልእክተኛው በመምጣት ላይ ወዳለው ጭፍራ ደርሶአል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ሲል አስረዳ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልእክተኛውም ጋልቦ ሄዶ ኢዩን “ንጉሡ አመጣጥህ በወዳጅነት እንደ ሆነ ማወቅ ይፈልጋል” ሲል ጠየቀው። ኢዩም “አንተ ከሰላም ጋር ምን ግንኙነት አለህ? ይልቅስ ወደ ኋላ አልፈህ ተከተለኝ!” ሲል መለሰለት። በከተማይቱም መጠበቂያ ግንብ ላይ የነበረው ዘብ “መልእክተኛው በመምጣት ላይ ወዳለው ጭፍራ ደርሶአል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ሲል አስረዳ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈረሰኛውም ሊገናኘው ሄዶ “ንጉሡ እንዲህ ይላል ‘ሰላም ነውን?’” አለ። ኢዩም “አንተ ከሰላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ አልፈህ ተከተለኝ፤” አለ። ሰላዩም “መልእክተኛው ደረሰባቸው፤ ነገር ግን አልተመለሰም፤” ብሎ ነገረው። |
ሰላይም ያያቸው ዘንድ በኢይዝራኤል ግንብ ላይ ቆመ፤ ሲመጡም የእነኢዩን አቧራ አየ። “እነሆም፥ አቧራ አያለሁ” አለ። ኢዮራምም፥ “ይገናኛቸው ዘንድ አንድ ፈረሰኛ ይሂድ፤ እርሱም፦ ሰላም ነውን? ይበላቸው” አለ።
ሁለተኛውንም ፈረሰኛ ሰደደ፤ ወደ እነርሱም ደርሶ ንጉሡ እንዲህ ይላል፥ “ሰላም ነውን?” አላቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመልሰህ ተከተለኝ” አለ።
ኢዮራምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ፥ ሰላም ነውን?” አለ። እርሱም፥ “የእናትህ የኤልዛቤል ግልሙትናዋና መተቷ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ።
የሰላምን መንገድ አያውቁም፤ በመንገዳቸውም ፍርድ የለም፤ የሚሄዱበትም መንገድ ጠማማ ነው፤ ሰላምንም አያውቁም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰላሜን፥ ቸርነቴንና ምሕረቴን፥ ከዚህ ሕዝብ አስወግጄአለሁና ልቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፤ ታለቅስና ታዝንም ዘንድ አትሂድ።