አቤሴሎምም፥ “የመለከት ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፥ አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ” በሉ የሚሉ ጕበኞችን ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ላከ።
2 ነገሥት 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰሙም ጊዜ ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ፤ በሰገነቱ መውጫ እርከን ላይም ከእግሩ በታች አነጠፉት፥ መለከትም እየነፉ፥ “ኢዩ ነግሦአል” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ ሁሉም ቶሎ ብለው ልብሳቸውን እያወለቁ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ ከዚያም መለከት ነፍተው፣ “ኢዩ ነግሧል” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም ፈጥነው ልባሳቸውን ወሰዱ፤ በሰገነቱ መሰላል እርከን ላይ ከእግሩ በታች አነጠፉት፤ ቀንደ መለከትም እየነፉ፥ “ኢዩ ነግሦአል!” አሉ። |
አቤሴሎምም፥ “የመለከት ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፥ አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ” በሉ የሚሉ ጕበኞችን ወደ እስራኤል ነገድ ሁሉ ላከ።
እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ጠቦቶችን፥ በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊቱን አለቃ ኢዮአብን፥ ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፤ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ፦ አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ ይላሉ።
በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በእስራኤል ላይ ቀብተው ያንግሡት፤ መለከትም ነፍታችሁ፦ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ በሉ።
ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የዘይቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባ፤ መለከትም ነፋ፤ ሕዝቡም ሁሉ፥ “ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ” አሉ።
የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
እነሆም፥ ንጉሡን እንደ ተለመደው በዓምዱ አጠገብ ቆሞ፥ ከንጉሡም ጋር መዘምራንና መለከተኞች ቆመው አየች፤ የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎአቸው መለከት ይነፉ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው፥ ዐመፅ ነው፥” ብላ ጮኸች።
እነርሱም፥ “ዋሸኸን፤ ነገር ግን ንገረን” አሉት፤ ኢዩም፦ ለጌታው ልጆች፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ ብሎ እንዲህና እንዲህ ነገረኝ” አላቸው።
ሙሴና አሮን በክህነታቸው ቅዱሳን ናቸውና ሳሙኤልም ስሙን ከሚጠሩት ጋራ፤ እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።