La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 8:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም የሞ​ተ​ውን ሕፃን እንደ አስ​ነሣ ለን​ጉሡ ሲና​ገር፥ እነሆ፥ ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላት ያች ሴት መጥታ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ወደ ንጉሥ ጮኸች፥ ግያ​ዝም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤል​ሳ​ዕም ያስ​ነ​ሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኤልሳዕ ልጇን ከሞት ያስነሣላት ሴት ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ለማመልከት ወደ ንጉሡ ዘንድ የቀረበችውም፣ ኤልሳዕ የሞተውን ልጅ እንዴት እንዳስነሣ ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ወቅት ነበር። ግያዝም፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣው ልጇም ይህ ነው” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኤልሳዕ የሞተ ሰው ማስነሣቱን ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ጊዜ ሴቲቱ መጥታ አቤቱታዋን ለንጉሡ አቀረበች፤ ግያዝ “ንጉሥ ሆይ! ሴትዮዋ እነሆ፥ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣውም ልጇ ይሄ ነው!” በማለት ለንጉሡ አስረዳ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኤልሳዕ የሞተ ሰው ማስነሣቱን ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ጊዜ ሴቲቱ መጥታ አቤቱታዋን ለንጉሡ አቀረበች፤ ግያዝ “ንጉሥ ሆይ! ሴትዮዋ እነሆ፥ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣውም ልጅዋ ይሄ ነው!” በማለት ለንጉሡ አስረዳ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም የሞተውን እንደ አስነሣ ለንጉሡ ሲናገር፥ እነሆ፥ ልጅዋን ያስነሣላት ሴት ስለ ቤትዋና ስለ መሬትዋ ወደ ንጉሥ ጮኸች፤ ግያዝም “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕም ያስነሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 8:5
16 Referencias Cruzadas  

ለኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ለና​ቡቴ በሰ​ማ​ርያ ንጉሥ በአ​ክ​ዓብ ቤት አጠ​ገብ የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው።


ሎሌ​ው​ንም ግያ​ዝን፥ “ይህ​ችን ሱማ​ና​ዊት ጥራ” አለው። በጠ​ራ​ትም ጊዜ በፊቱ ቆመች።


ተመ​ል​ሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲ​ህና ወዲያ ተመ​ላ​ለሰ፤ ደግ​ሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕ​ፃኑ ላይ ተጋ​ደመ፤ ከዚ​ያም በኋላ ሕፃኑ ዐይ​ኖ​ቹን ከፈተ።


ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ነቢዩ ኤል​ሳዕ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በእ​ል​ፍ​ኝህ ውስጥ ሆነህ የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንና ቃል​ህን ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እርሱ ይነ​ግ​ረ​ዋል፤” አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በቅ​ጥር ላይ ሲመ​ላ​ለስ አን​ዲት ሴት፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ርዳኝ” ብላ ወደ እርሱ ጮኸች።


ንጉ​ሡም ሴቲ​ቱን ጠየ​ቃት፤ እር​ስ​ዋም ነገ​ረ​ችው። ንጉ​ሡም ከባ​ለ​ሟ​ሎቹ አን​ዱን ሰጣት፤ “እህ​ል​ዋ​ንና ገን​ዘ​ብ​ዋን ሁሉ ሀገ​ሩን ከተ​ወች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሄደ ቦታ​ዋን ሁሉ መል​ስ​ላት” አለው።


ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች።


ኃጥእ ለክፉ ቀን ይጠበቃል።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ሩጫ ለፈ​ጣ​ኖች፥ ጦር​ነ​ትም ለኀ​ያ​ላን፥ እን​ጀ​ራም ለጠ​ቢ​ባን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች፥ ሞገ​ስም ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ዳ​ል​ሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገ​ና​ኛ​ቸ​ዋል።


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


ሄደችም፥ ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፣ እንደ አጋጣሚውም የአቤሜሌክ ወገን ወደ ነበረው ወደ ቦዔዝ እርሻ ደረሰች።


ሳኦ​ልም የዳ​ዊት ድምፅ እንደ ሆነ ዐውቆ፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አዎ እኔ ባሪ​ያህ ነኝ” አለው።