ያም ሎሌ ለኤልሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግዚአብሔር በሰማይ የእህል ሿሿቴ ቢያወርድ ይህ ነገር ይሆናልን?” ብሎ ነበር፤ ኤልሳዕም፥ “እነሆ፥ በዐይኖችህ ታየዋለህ፥ ከዚያም አትቀምስም” ብሎት ነበር።
2 ነገሥት 7:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ሆነ፤ ሕዝቡም በበሩ ረገጠውና ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በበሩ መተላለፊያ ላይ ሕዝቡ ረጋግጦት ስለ ሞተም፣ የተነገረበት በትክክል ደረሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ያ አገልጋይ በሰማርያ ከተማ ቅጽር በር ላይ ሕዝብ ረጋግጦት ለመሞት የበቃው ይህ ትንቢት ስለ ተፈጸመበት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ያ አገልጋይ በሰማርያ ከተማ ቅጽር በር ላይ ሕዝብ ረጋግጦት ለመሞት የበቃው ይህ ትንቢት ስለ ተፈጸመበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ደረሰበት፤ ሕዝቡም በበሩ ረገጠውና ሞተ። |
ያም ሎሌ ለኤልሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግዚአብሔር በሰማይ የእህል ሿሿቴ ቢያወርድ ይህ ነገር ይሆናልን?” ብሎ ነበር፤ ኤልሳዕም፥ “እነሆ፥ በዐይኖችህ ታየዋለህ፥ ከዚያም አትቀምስም” ብሎት ነበር።
ኤልሳዕም ልጅዋን ያስነሣላትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነሥተሽ ሂጂ፤ በምታገኚውም ስፍራ ተቀመጪ፤ እግዚአብሔር በምድር ራብን ጠርቶአልና፤ ሰባት ዓመትም በምድር ላይ ይቆያል” ብሎ ተናገራት።
ማልደውም ተነሡ፤ ወደ ቴቁሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወጡም ኢዮሣፍጥ ቆመና፥ “ይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ በነቢዩም እመኑ፤ ነገሩም ይቀናላችኋል” አለ።
የባርያውን ቃል ያጸናል፤ የመልእክተኞቹንም ምክር ይፈጽማል። ኢየሩሳሌምን፦ የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፤ የይሁዳንም ከተሞች ትታነጻላችሁ፤ ምድረ በዳዎችዋም ይለመልማሉ፤” ይላል፤
እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን፥ “በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር ይህን ማኅበር ይዛችሁ አትገቡም” አላቸው።