በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስክ ታላቃቸው ድረስ ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ ደጃፉንም ሲፈልጉ ደከሙ፤ አጡትም።
2 ነገሥት 6:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እርሱም በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ፥ “አቤቱ፥ እነዚህን ሰዎች አሳውራቸው” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ቃል አሳወራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሶርያውያንም ወርደው ወደ እርሱ ሲመጡ ኤልሳዕ፣ “ይህን ሕዝብ ዕውር አድርገው” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ስለዚህ ኤልሳዕ በጠየቀው መሠረት እግዚአብሔር ዕውር አደረጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሶርያውያንም ወደ እርሱ በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች እንዲታወሩ አድርግ!” ብሎ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕን ጸሎት በመስማት፥ ዐይኖቻቸው እንዲታወሩ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሶርያውያንም ወደ እርሱ በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች እንዲታወሩ አድርግ!” ብሎ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕን ጸሎት በመስማት፥ ዐይኖቻቸው እንዲታወሩ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እርሱም በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ “ይህን ሕዝብ ዕውር ታደርገው ዘንድ እለምንሃለሁ፤” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ቃል ዕውር አደረጋቸው። |
በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስክ ታላቃቸው ድረስ ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ ደጃፉንም ሲፈልጉ ደከሙ፤ አጡትም።
ኤልሳዕም፥ “መንገዱ በዚህ አይደለም፥ ከተማዪቱም ይህች አይደለችም፤ የምትሹትን ሰው አሳያችሁ ዘንድ ተከተሉኝ” አላቸው፤ ወደ ሰማርያም ወሰዳቸው።
ነገር ግን የይሁዳን ልጆች ይቅር እላቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸውም እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት ወይም በሰይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠረገላ፥ ወይም በፈረሶች፥ ወይም በፈረሰኞች የማድናቸው አይደለም” አለው።
በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፈረስን ሁሉ በድንጋጤ፥ ተቀማጭንም በእብድነት እመታለሁ፣ ዓይኖቼንም በይሁዳ ላይ እከፍታለሁ፥ የአሕዛብንም ፈረሶች ሁሉ በዕውርነት እመታለሁ።
“በዐይናቸው አይተው፥ በልባቸውም አስተውለው እንዳይመለሱና እንዳልፈውሳቸው ዐይኖቻቸው ታወሩ፤ ልባቸውም ደነደነ።”
እነሆ፥ አሁን የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዕውርም ትሆናለህ፤ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” ወዲያውኑም ታወረ፤ ጨለማም ዋጠው፤ የሚመራውም ፈለገ።