እርሱም፥ “እኔ ደግሞ እንዳንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም፦ እንጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።
2 ነገሥት 5:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ሁሉ ደኅና ነው፦ አሁን ከነቢያት ወገን የሆኑ ሁለት ጐልማሶች ከተራራማው ከኤፍሬም ሀገር ወደ እኔ መጥተዋልና፤ አንድ መክሊት ብርና ሁለት መለወጫ ልብስ ትሰጣቸው ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ጌታዬ ላከኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግያዝም፣ “ሁሉም ደኅና ነው፤ ግን ጌታዬ፣ ‘ከነቢያት ማኅበር ሁለት ወጣቶች ከኰረብታማው አገር ከኤፍሬም ወደ እኔ አሁን በድንገት ስለ መጡ፣ እባክህ፤ አንድ መክሊት ብርና ሁለት ሙሉ ልብስ ስጣቸው ብለህ ንገር’ ብሎ ልኮኛል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግያዝም “መምጣትስ በደኅና ነው የመጣሁት፤ ነገር ግን ጌታዬ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖሩ ሁለት የነቢያት ጉባኤ አባላት ድንገት በእንግድነት ስለ መጡበት፥ ሦስት ሺህ ብርና ሁለት መቀየሪያ ልብስ እንድትሰጣቸው እነግርህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል” ሲል መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግያዝም “መምጣትስ በደኅና ነው የመጣሁት፤ ነገር ግን ጌታዬ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖሩ ሁለት የነቢያት ጒባኤ አባላት ድንገት በእንግድነት ስለ መጡበት፥ ሦስት ሺህ ብርና ሁለት መቀየሪያ ልብስ እንድትሰጣቸው እነግርህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “ደኅና ነው፤ ‘አሁን ከነቢያት ወገን የሆኑት ሁለት ጕልማሶች ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ወደ እኔ መጥተዋል፤ አንድ መክሊት ብርና ሁለት መለወጫ ልብስ ትሰጣቸው ዘንድ እለምንሃለሁ፤’ ብሎ ጌታዬ ላከኝ፤” አለ። |
እርሱም፥ “እኔ ደግሞ እንዳንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም፦ እንጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።
በኢያሪኮም የነበሩት የነቢያት ልጆች ኤልሳዕ ወደ እነርሱ ሲመጣ ባዩት ጊዜ፥ “የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ዐርፎአል” አሉ። ሊገናኙትም መጥተው በፊቱ በምድር ላይ ሰገዱለት።
በቤቴልም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ መጥተው፥ “እግዚአብሔር ጌታህን ከአንተ ለይቶ ዛሬ እንደሚወስደው ዐውቀሃልን?” አሉት። እርሱም፥ “አዎን፥ ዐውቄአለሁ፤ ዝም በሉ” አላቸው።
ወደ ኢያሪኮም ደረሱ፤ በኢያሪኮም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ቀርበው፥ “እግዚአብሔር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው ዐውቀሃልን?” አሉት። እርሱም፥ “አዎን፥ ዐውቄአለሁ፤ ዝም በሉ” አላቸው።
አሁንም ሩጥና ተቀበላት፤ በደኅናሽ ነውን? ባልሽ ደኅና ነውን? ልጅሽስ ደኅና ነውን? በላት” አለው። እርስዋም፥ “ደኅና ነው” አለች።
ግያዝም ንዕማንን ተከተለው፤ ንዕማንም ዘወር ብሎ ወደ እርሱ ሲሮጥ ባየው ጊዜ ሊገናኘው ከሰረገላው ወርዶ፥ “ሁሉ ደኅና ነውን?” አለው።
ከዚህም በኋላ ገብቶ፥ በጌታው ፊት ቆመ፤ ኤልሳዕም፥ “ግያዝ ሆይ፥ ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም፥ “እኔ አገልጋይህ ወዴትም አልሄድሁም” አለ።
የሶርያም ንጉሥ ንዕማንን፥ “ሂድ፥ ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እልካለሁ” አለው። እርሱም ሄደ፤ ዐሥርም መክሊት ብር፥ ስድስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥርም መለወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።
እጃችሁ በደም ጣታችሁም በኀጢአት ተሞልትዋል፤ ከንፈራችሁም ዐመፅን ተናግሮአል፤ ምላሳችሁም ኀጢአትን አሰምቶአል።
“ምላሳቸውን ለሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥” ይላል እግዚአብሔር።
እያንዳንዱ በባልንጀራው ላይ ይሣለቃል በእውነትም አይናገርም፤ ሐሰት መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፤ በደሉ መመለስንም እንቢ አሉ።
እናንተስ ከአባታችሁ ከሰይጣን ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፈቃድ ልታደርጉ ትወዳላችሁ፤ እርሱ ከጥንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእውነትም አይቆምም፤ በእርሱ ዘንድ እውነት የለምና፤ ሐሰትንም በሚናገርበት ጊዜ ከራሱ አንቅቶ ይናገራል፤ ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰትም አባት ነውና።
የአሮንም ልጅ ሊቀ ካህናቱ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራማውም በኤፍሬም ሀገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓት መሬት ቀበሩት።
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”
ሶምሶንም አላቸው፥ “እንቆቅልሽ ልስጣችሁ፤ በሰባቱም በበዓሉ ቀኖች ውስጥ ፈትታችሁ ብትነግሩኝ፥ ሠላሳ የበፍታ ቀሚስና ሠላሳ ልውጥ ልብስ እሰጣችኋለሁ፤