Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 5:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ንዕ​ማ​ንም፥ “ሁለት የብር መክ​ሊት ውሰድ” አለው፤ ሁለ​ቱ​ንም መክ​ሊት ብር ተቀ​ብሎ በሁ​ለት ከረ​ጢት ውስጥ ጨመ​ረና ከሁ​ለት መለ​ወጫ ልብስ ጋር ለሁ​ለት ሎሌ​ዎቹ አስ​ያዘ፤ እነ​ር​ሱም ተሸ​ክ​መው በፊቱ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ንዕማንም፣ “እባክህ፤ ሁለት መክሊት ውሰድ” በማለት ግያዝን አስጨንቆ ለመነው። ከዚያም ሁለቱን መክሊት ብር፣ በሁለት ከረጢት ውስጥ አስሮ ሁለት ሙሉ ልብስ ጨምሮ ለሁለት አገልጋዮቹ አስያዘ፤ እነርሱም ያን ተሸክመው ከግያዝ ፊት ፊት ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ንዕማንም “እንግዲያውስ እባክህ ስድስት ሺህ ብር ልስጥ” ሲል መለሰለት፤ በዚህም አሳቡ በመጽናት ብሩን በሁለት ከረጢት ሞልቶ ከሁለት መለወጫ ልብሶች ጋር በሁለት አገልጋዮች አስይዞ ከግያዝ ቀድመው በፊት በፊቱ እንዲሄዱ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ንዕማንም “እንግዲያውስ እባክህ ስድስት ሺህ ብር ልስጥ” ሲል መለሰለት፤ በዚህም አሳቡ በመጽናት ብሩን በሁለት ከረጢት ሞልቶ ከሁለት መለወጫ ልብሶች ጋር በሁለት አገልጋዮች አስይዞ ከግያዝ ቀድመው በፊት በፊቱ እንዲሄዱ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ንዕማንም “ሁለት መክሊት ትወስድ ዘንድ ይፈቀድልህ፤” አለ፤ ግድ አለውም፤ ሁለቱንም መክሊት ብር በሁለት ከረጢት ውስጥ አሰረና ከሁለት መለወጫ ልብስ ጋር ለሁለት ሎሌዎቹ አስያዘ፤ እነርሱም ተሸክመው በፊቱ ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 5:23
9 Referencias Cruzadas  

በአ​ነ​ጋ​ገ​ሩም ሊያ​ስ​ቱ​ትና ሊያ​ጣ​ሉት ያደ​ቡ​በት ነበር።


ተባ​ትና እን​ስት አን​በሳ፥ እፉ​ኝ​ትም፥ ነዘር እባ​ብም፥ በሚ​ወ​ጡ​ባት በመ​ከ​ራና በጭ​ን​ቀት ምድር በኩል ብል​ጽ​ግ​ና​ቸ​ውን በአ​ህ​ዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በግ​መ​ሎች ሻኛ ላይ እየ​ጫኑ ወደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙ​አ​ቸው ሕዝብ ይሄ​ዳሉ።


በሣ​ጥ​ኑም ውስጥ የተ​ገ​ኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የን​ጉሡ ጸሓ​ፊና የካ​ህ​ናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ ቈጥ​ረው በከ​ረ​ጢት ውስጥ ያኖ​ሩት ነበር።


ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ፥ “አንተ ደግሞ ከእኛ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ለመ​ሄድ ና” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “እሽ እኔም እመ​ጣ​ለሁ” አለ።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አል​ቀ​በ​ልም” አለ። ይቀ​በ​ለ​ውም ዘንድ ግድ አለው፤ እርሱ ግን እንቢ አለ።


እስ​ኪ​ያ​ፍ​ራ​ቸ​ውም ድረስ ግድ ባሉት ጊዜ፥ “ላኩ” አለ፤ አም​ሳም ሰዎች ላኩ፤ ሦስት ቀንም ፈል​ገው አላ​ገ​ኙ​ትም።


ሚስቱ ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “አሁ​ንም አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሆነህ እን​ደ​ዚህ ታደ​ር​ጋ​ለ​ህን? ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ብላ፤ ራስ​ህ​ንም አጽና፤ ልብ​ህም ደስ ይበ​ላት፤ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ው​ንም የና​ቡ​ቴን የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለ​ችው።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ ንዕ​ማ​ንን፥ “ሂድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ደብ​ዳቤ እል​ካ​ለሁ” አለው። እር​ሱም ሄደ፤ ዐሥ​ርም መክ​ሊት ብር፥ ስድ​ስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥ​ርም መለ​ወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።


ከወ​ደ​ድ​ኸ​ኝስ ይህ​ችን ያመ​ጣ​ሁ​ል​ህን በረ​ከ​ቴን ተቀ​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ል​ኛ​ልና፥ ለእ​ኔም ብዙ አለ​ኝና።” እስ​ኪ​ቀ​በ​ለ​ውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀ​በ​ለ​ውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios