በኢዮአብ ራስ ላይና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይምጣበት፤ በኢዮአብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለበት ወይም ለምጻም ወይም አንካሳ ወይም በሰይፍ የሚወድቅ ወይም እንጀራ የሌለው ሰው አይታጣ።”
2 ነገሥት 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ፥ በጌታው ዘንድ ታላቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰውዬውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ንዕማን የሶርያ ንጉሥ ጦር አዛዥ ነበረ፤ እግዚአብሔር በዚህ ሰው አማካይነት፣ ሶርያ ድልን እንድትጐናጸፍ ስላደረጋት በጌታው ዘንድ ታላቅና የተከበረ ሰው ነበር። ጀግና ወታደር ቢሆንም ለምጽ ወጥቶበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቆዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በንዕማን አማካይነት ለሶርያ ሠራዊት ድልን ስለ አጐናጸፈ፥ የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ እጅግ የተከበረና የተወደደ ባለሟል ነበር፤ ታዲያ ንዕማን ጀግና ወታደር ሆኖ ሳለ፥ በቈዳ በሽታ ይሠቃይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማን እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ነበረ፤ ደግሞም ጽኑዕ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ። |
በኢዮአብ ራስ ላይና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይምጣበት፤ በኢዮአብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለበት ወይም ለምጻም ወይም አንካሳ ወይም በሰይፍ የሚወድቅ ወይም እንጀራ የሌለው ሰው አይታጣ።”
ከዚህም በኋላ አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፤ ኤልሳዕ ወደ ሱማን አለፈ፤ በዚያም ታላቅ ሴት ነበረች፤ እንጀራም ይበላ ዘንድ አቆመችው፤ በዚያም ባለፈ ቍጥር እንጀራ ሊበላ ወደዚያ ይገባ ነበር።
ከሶርያውያንም ጋር ወደ ሰልፍ በወጣ ጊዜ ከእስራኤል ምድር ታናሽ ብላቴና ሴት ማረከ፤ ለሚስቱም አገልጋይ አደረጋት።
ነገር ግን የንዕማን ለምጽ በአንተና በዘርህ ላይ፥ ለዘለዓለም ይመለስ” አለው። እንደ በረዶም ለምጻም ሆኖ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።
እግዚአብሔርም በግብፃውያን ፊት ለሕዝቡ ሞገስን ሰጠ፤ አዋሱአቸውም፤ ይህ ሙሴም በግብፃውያንና በፈርዖን፥ በሹሞቹም ፊት እጅግ የከበረ ሰው ነበረ።
በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም ብዙ ለምጻሞች በእስራኤል ውስጥ ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነዚያ አንድ እንኳን አልነጻም።”
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ከሰማይ ካልተሰጠህ በቀር በእኔ ላይ አንዳች ሥልጣን የለህም፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢኣት አለበት” አለው።
ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር እንዳዘዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተራራማውም ሀገር ወደ አሉ ከተሞች አልደረስንም።