የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
2 ነገሥት 4:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም ግያዝን፥ “ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬንም በእጅህ ይዘህ ሂድ፤ ሰውም ብታገኝ ሰላም አትበል፤ እርሱም ሰላም ቢልህ አትመልስለት፤ በትሬንም በሕፃኑ ፊት ላይ አኑር” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕም ግያዝን፣ “እንግዲህ ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬን ያዝና ሩጥ፤ መንገድ ላይ ሰው ብታገኝ ሰላም አትበል፤ ማንም ሰው ሰላም ቢልህ መልስ አትስጥ፤ በትሬንም በልጁ ፊት ላይ አድርግ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም ወደ ግያዝ መለስ ብሎ “በፍጥነት ተነሥና የእኔን ምርኲዝ ይዘህ ሂድ! ለአንድም ሰው ሰላምታ ለመስጠት እንኳ በመንገድ አትቁም፤ ማንም ሰው ሰላምታ ቢሰጥህ አጸፋውን ለመመለስ ጊዜ አታጥፋ፤ በቀጥታ ወደ ቤት ሄደህ የእኔን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኑር!” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም ወደ ግያዝ መለስ ብሎ “በፍጥነት ተነሥና የእኔን ምርኲዝ ይዘህ ሂድ! ለአንድም ሰው ሰላምታ ለመስጠት እንኳ በመንገድ አትቁም፤ ማንም ሰው ሰላምታ ቢሰጥህ አጸፋውን ለመመለስ ጊዜ አታጥፋ፤ በቀጥታ ወደ ቤት ሄደህ የእኔን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኑር!” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግያዝንም “ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬንም በእጅህ ይዘህ ሂድ፤ ሰውም ብታገኝ ሰላም አትበል፤ እርሱም ሰላም ቢልህ አትመልስለት፤ በትሬንም በሕፃኑ ፊት ላይ አኑር፤” አለው። |
የእግዚአብሔርም እጅ በኤልያስ ላይ ነበረች፤ ወገቡንም ታጥቆ ወደ ኢይዝራኤል እስኪገባ ድረስ በአክዓብ ፊት ይሮጥ ነበር።
በራሱ ላይ ያረፈችውን የኤልያስን መጠምጠሚያ ወስዶ ውኃውን መታባት፦ ውኃው ግን አልተከፈለም፤ እርሱም፥ “የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው? እንዴትስ ነው?” አለ። ከዚህም በኋላ ውኃውን በመታ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።
ኤልያስም መጠምጠሚያውን ወስዶ ጠቀለለው፤ የዮርዳኖስንም ውኃ መታበት፤ ውኃውም ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፤ ሁለቱም በደረቅ ተሻገሩ። ወጥተውም በምድረ በዳው ቆሙ።
ነቢዩም ኤልሳዕ ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፥ “ወገብህን ታጥቀህ ይህን የዘይት ቀንድ በእጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገለዓድም ሂድ።
አንተም በትርህን አንሣ፤ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ።
ከልብሱ ዘርፍና ከመጠምጠሚያዉ ጫፍ ቈርጠው እየወሰዱ በድውያኑ ላይ ያኖሩት ነበር፤ እነርሱም ይፈወሱ ነበር፤ ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።
ስሙን በማመን ይህን የምታዩትንና የምታውቁትን የእርሱ ስም አጸናው፤ እርሱንም በማመን በፊታችሁ ይህን ሕይወት ሰጠው።