ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ቀርበውኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች ቸርነትን አድርግላቸው። በማዕድህም ከሚበሉት መካከል ይሁኑ።
2 ነገሥት 25:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀለቡንም ሁልጊዜ ከንጉሡ ቤት ይቀበል ነበር፤ በሕይወቱም ዘመን ሁሉ የዘወትር ቀለቡን ዕለት ዕለት ይሰጡት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ለዮአኪን እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ የዕለት ቀለቡን ይሰጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኖረበት ዘመን ሁሉ በየቀኑ ለማናቸውም ለሚያስፈልገው ነገር ያውለው ዘንድ የዘወትር ቀለብ ይሰጠው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኖረበት ዘመን ሁሉ በየቀኑ ለማናቸውም ለሚያስፈልገው ነገር ያውለው ዘንድ የዘወትር ቀለብ ይሰጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ የዘወትር ቀለብ ዕለት ዕለት ይሰጠው ነበር። |
ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ቀርበውኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች ቸርነትን አድርግላቸው። በማዕድህም ከሚበሉት መካከል ይሁኑ።
እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፤ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።
አንተንም፥ የወለደችህን እናትህንም ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ ሀገር እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ።
በዚያም ወራት ደቀ መዛሙርት በበዙ ጊዜ ከግሪክ የመጡ ደቀ መዛሙርት በአይሁድ ምእመናን ላይ አንጐራጐሩባቸው፤ የዕለት የዕለቱን ምግብ ሲያካፍሉ ባልቴቶቻቸውን ቸል ይሉባቸው ነበርና።