ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና።
2 ነገሥት 23:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ሙሴም ሕግ ሁሉ በፍጹም ልቡ በፍጹምም ነፍሱ በፍጹምም ኀይሉ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ ከእርሱ አስቀድሞ አልነበረም፤ እንደ እርሱም ያለ ንጉሥ ከእርሱ በኋላ አልተነሣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱ፣ በፍጹም ኀይሉ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ፣ እንደ ኢዮስያስ ያለ ንጉሥ፣ ከርሱ በፊትም ሆነ ከርሱ በኋላ ፈጽሞ አልተነሣም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለኦሪት ሕግ በመታዘዝ በፍጹም ልቡ፥ በፍጹም ነፍሱና በፍጹም ኃይሉ እግዚአብሔርን ያገለገለ እንደ ኢዮስያስ ያለ ንጉሥ ከእርሱም በፊት ሆነ ከእርሱ ወዲህ ከቶ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኦሪት ሕግ በመታዘዝ በፍጹም ልቡ፥ በፍጹም ነፍሱና በፍጹም ኀይሉ እግዚአብሔርን ያገለገለ እንደ ኢዮስያስ ያለ ንጉሥ ከእርሱም በፊት ሆነ ከእርሱ ወዲህ ከቶ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ሙሴም ሕግ ሁሉ በፍጹም ልቡ በፍጹምም ነፍሱ በፍጹምም ኀይሉ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ ከእርሱ አስቀድሞ አልነበረም፤ እንደ እርሱም ያለ ንጉሥ ከእርሱ በኋላ አልተነሣም። |
ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና።
ይኸውም እግዚአብሔር ስለ እኔ፦ ‘ልጆችህ መንገዳቸውን ቢጠብቁ፥ በፊቴም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በእውነት ቢሄዱ ከእስራኤል ዙፋን ሰው አይጠፋም’ ብሎ የተናገረውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።
በማረኩአቸው በጠላቶቻቸው ሀገር ሳሉ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠሃት ወደ ምድራቸው ወደ መረጥሃትም ከተማ ለስምህም ወደ ሠራሁት ቤት ቢጸልዩ፥
በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ታመነ፤ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ከይሁዳ ነገሥታት ሁሉ እርሱን የሚመስል አልነበረም።
ንጉሡም በዓምደ ወርቁ አጠገብ ቆሞ እግዚአብሔርን ይከተሉ ዘንድ፥ ትእዛዙንና ምስክሩንም ሥርዐቱንም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይጠብቁ ዘንድ፥ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል ያጸኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቃል ኪዳን ጸኑ።
በእግዚአብሔርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ፥ ፍርዱንም፥ ሥርዐቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ርግማንንና መሐላን አደረጉ።
በአባትህ ዝግባ አዳራሽ ስለ ሠራህ በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ አይበላና አይጠጣም ነበርን? ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር።
ሙሴ ኦሪትን ሰጥቶአችሁ የለምን? ከእናንተ አንዱ ስንኳ ኦሪትን የሚያደርግ የለም፤ እንግዲህ ልትገድሉኝ ለምን ትሻላችሁ?”
ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ፤ በመከራህም ጊዜ በልብህም ሁሉ፥ በነፍስህም ሁሉየፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።