2 ነገሥት 23:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ካህኑ ኬልቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈውን የሕጉን ቃል ያጸና ዘንድ፥ መናፍስት ጠሪዎቹንና ጠንቋዮቹን ተራፊምንና ጣዖታትንም በይሁዳ ሀገርና በኢየሩሳሌም የተገኘውን ርኵሰት ሁሉ ኢዮስያስ አስወገደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በቀር ኢዮስያስ ሙታን አነጋጋሪዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን፣ የየቤተ ሰቡ ሰውን አማልክት፣ ጣዖታትን እንዲሁም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የተገኙትን ሌሎች አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ አስወገደ፤ ይህን ያደረገውም ካህኑ ኬልቅያስ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈው የሕጉ ቃል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊቀ ካህናቱ ሒልቂያ በቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው ሕግ ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው በማሰብ፥ ንጉሥ ኢዮስያስ ከኢየሩሳሌምና ከሌላውም የይሁዳ ከተማ ሁሉ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ሁሉ የቤተሰብ አማልክትን፥ ጣዖቶችንና ሌሎችንም አረማዊ የአምልኮ መፈጸሚያ ዕቃዎችን ሁሉ አስወገደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊቀ ካህናቱ ሒልቂያ በቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው ሕግ ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው በማሰብ፥ ንጉሥ ኢዮስያስ ከኢየሩሳሌምና ከሌላውም የይሁዳ ከተማ ሁሉ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ሁሉ የቤተሰብ አማልክትን፥ ጣዖቶችንና ሌሎችንም አረማዊ የአምልኮ መፈጸሚያ ዕቃዎችን ሁሉ አስወገደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ካህኑ ኬልቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈውን የሕጉን ቃል ያጸና ዘንድ፥ መናፍስት ጠሪዎቹንና ጠንቋዮቹን ተራፊምንና ጣዖታትንም በይሁዳ አገርና በኢየሩሳሌም የተገኘውን ርኵሰት ሁሉ ኢዮስያስ አስወገደ። |
“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ከእርሱ በፊት የነበሩ አሞራውያን ከሠሩት ሁሉ ይልቅ ይህን ክፉ ርኵሰት አድርጎአልና፥ ይሁዳንም ደግሞ በጣዖታቱ አስቶአልና፥
አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች መልሶ ሠራ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለበዓል መሠዊያን ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከለ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገደ አመለካቸውም።
ልጁንም በእሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ በእግዚአብሔርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ፤ ኣስቈጣውም።
የግብፅም መንፈስ በውስጣቸው ትደነግጣለች፤ ምክራቸውን አጠፋለሁ፤ እነርሱም አማልክቶቻቸውንና ጣዖቶቻቸውን፥ ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ይጠይቃሉ።
የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ምሥዋዕ፤ ያለ ካህንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤
“ወደ መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች አትሂዱ፤ እንዳትረክሱባቸውም አትፈልጉአቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
“ወንድ ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ፥ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በድንጋይም ይውገሩአቸው፤ በደለኞች ናቸውና።”