2 ነገሥት 22:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሓፊው ሳፋንም ለንጉሡ፥ “ካህኑ ኬልቅያስ የሕግ መጽሐፍ ሰጥቶኛል” ብሎ ነገረው። ሳፋንም በንጉሡ ፊት አነበበው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ጸሓፊው ሳፋን ለንጉሡ፣ “ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ መጽሐፍ ሰጥቶኛል” ብሎ ነገረው። ሳፋንም ለንጉሡ ከመጽሐፉ አነበበለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ቀጠል በማድረግ፥ “ካህኑ ሒልቂያ አግኝቶ የሰጠኝ መጽሐፍ ይኸው” ብሎ ለንጉሡ አነበበለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ቀጠል በማድረግ፥ “ካህኑ ሒልቂያ አግኝቶ የሰጠኝ መጽሐፍ ይኸው” ብሎ ለንጉሡ አነበበለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጸሐፊው ሳፋንም ለንጉሡ “ካህኑ ኬልቅያስ መጽሐፍ ሰጥቶኛል፤” ብሎ ነገረው። ሳፋንም በንጉሡ ፊት አነበበው። |
ጸሓፊውም ሳፋን ወደ ንጉሡ መጣ፤ ለንጉሡም፥ “በመቅደሱ የተገኘውን ገንዘብ አገልጋዮችህ አፈሰሱት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት ሥራ ለመሥራት ለተመደቡት ሰዎች ሰጡት” ብሎ ነገረው።
በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ በሕዝቡ ጆሮ አነበቡ፤ አሞናውያንና ሞዓባውያንም ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ለዘለዓለም እንዳይገቡ የሚል በዚያ አገኙ።
ከመጀመሪያውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉንም ሰባት ቀን ያህል አደረጉ፤ በስምንተኛውም ቀን እንደ ሕጋቸው ወጡ።
ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ የዋሁና ወደ ጸጥተኛው፥ ከቃሌም የተነሣ ወደሚንቀጠቀጥ ሰው ከአልሆነ በቀር ወደ ማን እመለከታለሁ?
በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ “የእግዚአብሔር ስም ይከብር ዘንድ፦ ደስታችሁም ይገለጥ ዘንድ፥ እነርሱም ያፍሩ ዘንድ የሚጠሏችሁንና የሚጸየፉአችሁን ወንድሞቻችን በሏቸው።
ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
ንጉሡም ክርታሱን ያመጣ ዘንድ ይሁዳን ላከ፤ እርሱም ከጸሓፊው ከኤሊሳማ ክፍል ወሰደው፤ ይሁዳም በንጉሡና በንጉሡ አጠገብ በቆሙት አለቆች ሁሉ ጆሮ አነበበው።
አንተ ግን ገብተህ ከአፌ የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል በጾም ቀን በእግዚአብሔር ቤት በሕዝቡ ጆሮ በክርታሱ አንብብ፤ ደግሞም ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው።