La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 14:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያን ጊዜም አሜ​ስ​ያስ፥ “ና እርስ በር​ሳ​ችን ፊት ለፊት እን​ተ​ያይ” ብሎ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮ​አ​ካዝ ልጅ ወደ ዮአስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም አሜስያስ የኢዩ የልጅ ልጅ፣ የኢዮአካዝ ልጅ ወደ ሆነው ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ዮአስ፣ “ናና ፊት ለፊት እንጋጠም” ሲል መልእክተኞች ላከበት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚህ በኋላ አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞች በመላክ “እንግዲህ ና ይዋጣልን!” ሲል ለጦርነት አነሣሣው፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞች በመላክ “እንግዲህ ና ይዋጣልን!” ሲል ለጦርነት አነሣሣው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያን ጊዜም አሜስያስ “ና፤ እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ፤” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞችን ላከ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 14:8
12 Referencias Cruzadas  

“ተነ​ሥ​ተህ በሰ​ማ​ርያ የሚ​ኖ​ረ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ አክ​ዓ​ብን ትገ​ናኝ ዘንድ ውረድ፤ እነሆ፥ ይወ​ር​ሰው ዘንድ በወ​ረ​ደ​በት በና​ቡቴ የወ​ይን ቦታ ውስጥ አለ።


የቀ​ረ​ውም የዮ​አስ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ከአ​ሜ​ስ​ያስ ጋር የተ​ዋ​ጋ​በት ኀይሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


አሜ​ስ​ያስ ግን አል​ሰ​ማም፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ዘመተ፤ እር​ሱና የይ​ሁዳ ንጉሥ አሜ​ስ​ያ​ስም በይ​ሁዳ ባለች በቤ​ት​ሳ​ሚስ ፊት ለፊት ተያዩ።


አሜ​ስ​ያ​ስም የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ሰዎች ከገ​ደለ በኋላ የሴ​ይ​ርን ልጆች አማ​ል​ክት አመጣ፤ የእ​ር​ሱም አማ​ል​ክት ይሆኑ ዘንድ አቆ​ማ​ቸው፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውና ይሠ​ዋ​ላ​ቸው ነበር።


ክፉ ሰው ከመሳደብ ጋር ክፋትን ይሠራል፤ ራሳቸውን የሚያውቁ ግን ብልሆች ናቸው።


የጠብ መጀመሪያ ውኃን መድፈን ነው። የጽድቅ መጀመሪያ በነገር መሠልጠንን ይሰጣል፥ የችጋር አበጋዝ ጠብና ክርክር ነው።


አላዋቂን ከንፈሮቹ ወደ ክፉ ያደርሱታል፥ የችኩል አፍም ሞትን ይጠራል።


ዐሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።


ይህ ሕዝብ ከእጄ በታች ቢሆን ኖሮ አቤ​ሜ​ሌ​ክን አሳ​ድ​ደው ነበር” አለ። አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም፥ “ሠራ​ዊ​ት​ህን አብ​ዝ​ተህ ና፤ ውጣ” አለው።