አክዓብም፥ “በምን አውቃለሁ?” አለ፤ እርሱም፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአውራጃዎቹ አለቆች ጐልማሶች” አለ፤ አክዓብም፥ “ውጊያውን ማን ይጀምራል?” አለ፤ እርሱም፥ “አንተ” አለው።
2 ነገሥት 10:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልእክተኛም መጥቶ፥ “የንጉሡን ልጆች ራስ ይዘው መጥተዋል” ብሎ ነገረው። ንጉሡም፥ “እስከ ነገ ድረስ በበሩ አደባባይ ሁለት ክምር አድርጋችሁ አኑሩአቸው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልእክተኛው እንደ ደረሰም፣ ለኢዩ፣ “የንጉሡን ልጆች ራስ አምጥተዋል” ብሎ ነገረው። ከዚያም ኢዩ፣ “በከተማዪቱ መግቢያ በር ላይ ሁለት ቦታ ከምራችሁ እስከ ነገ ጧት ድረስ አቈዩአቸው” ብሎ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዩ የአክዓብ ትውልድ ራሶች ተቆርጠው መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በከተማይቱ ቅጽር በር በሁለት ረድፍ ተከምረው እስከ ተከታዩ ቀን ጧት ድረስ እንዲቆዩ ትእዛዝ ሰጠ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዩ የአክዓብ ትውልድ ራሶች ተቈርጠው መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በከተማይቱ ቅጽር በር በሁለት ረድፍ ተከምረው እስከ ተከታዩ ቀን ጧት ድረስ እንዲቈዩ ትእዛዝ ሰጠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልእክተኛም መጥቶ “የንጉሡን ልጆች ራሶች ይዘው መጥተዋል፤” ብሎ ነገረው። እርሱም “እስከ ነገ ድረስ በበሩ አደባባይ ሁለት ክምር አድርጋችሁ አኑሩአቸው፤” አለ። |
አክዓብም፥ “በምን አውቃለሁ?” አለ፤ እርሱም፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በአውራጃዎቹ አለቆች ጐልማሶች” አለ፤ አክዓብም፥ “ውጊያውን ማን ይጀምራል?” አለ፤ እርሱም፥ “አንተ” አለው።
ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ የሀገሩ ሰዎች የንጉሡን ልጆች ሰባውን ሰዎች ይዘው ገደሉአቸው፤ ራሳቸውንም በቅርጫት አድርገው ወደ እርሱ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ።
በነጋውም ንጉሡ ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝቡንም ሁሉ፥ “እናንተ ንጹሓን ናችሁ፤ እነሆ፥ የጌታዬን ቤት የወነጀልሁ የገደልኋቸውም እኔ ነኝ፤ እነዚህንስ ሁሉ የገደለ ማን ነው?
በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሥጋው በእንጨት ላይ አይደር፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር እንዳታረክስ በእርግጥ በዚያው ቀን ቅበረው።