2 ነገሥት 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአክአብም የቤቱ አለቆች፥ የከተማዪቱም አለቆች፥ ሽማግሌዎቹና ልጆቹንም የሚያሳድጉ፥ “እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ ያዘዝኸንንም ሁሉ እናደርጋለን፤ የምናነግሠው ሰው የለም፤ የምትወድደውን አድርግ” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፣ የከተማዪቱ ገዥ፣ ሽማግሌዎችና የልጆቹ ሞግዚቶች፣ “እኛ የአንተው አገልጋዮች ነን፤ ትእዛዝህን ሁሉ እንፈጽማለን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ ደስ የሚያሰኝህን ሁሉ አንተው አድርግ” በማለት ይህን መልእክት ለኢዩ ላኩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊና የከተማይቱ ገዢ ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና ከአሳዳጊ ሞግዚቶች ጋር በመተባበር ለኢዩ “እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ አንተ የምታዘንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ነን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ አንተ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ሲሉ መልእክት ላኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊና የከተማይቱ ገዢ ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና ከአሳዳጊ ሞግዚቶች ጋር በመተባበር ለኢዩ “እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ አንተ የምታዘንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ነን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ አንተ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” ሲሉ መልእክት ላኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቤቱ አለቃ፥ የከተማይቱም አለቃ፥ ሽማግሌዎችና ልጆቹን የሚያሳድጉ “እኛ ባሪያዎችህ ነን፤ ያዘዝኸንንም ሁሉ እናደርጋለን፤ ንጉሥም በላያችን አናነግሥም፤ የምትወድደውን አድርግ፤” ብለው ወደ ኢዩ ላኩ። |
ከዚህም በኋላ ኢዩ፥ “ወገኖቼስ ከሆናችሁ፥ ነገሬንም ከሰማችሁ የጌታችሁን ልጆች ራስ ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይዝራኤል ወደ እኔ ይዛችሁ ኑ” ብሎ ሁለተኛ ደብዳቤ ጻፈላቸው። የንጉሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚያሳድጓቸው በከተማዪቱ ታላላቆች ዘንድ ነበሩ።
የይሁዳም ንጉሥ ሕዝቅያስ፥ “በድያለሁ፥ ከእኔ ተመለስ፤ የምትጭንብኝንም ሁሉ እሸከማለሁ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ለኪሶ መልእክተኞችን ላከ። የአሦርም ንጉሥ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ላይ ሦስት መቶ መክሊት ብርና ሠላሳ መክሊት ወርቅ ጫነበት።
አንተ ለአባቶቻቸው ወደ ማልህላቸው ምድር አደርሳቸው ዘንድ፦ ሞግዚት የሚጠባውን ልጅ እንድታቅፍ በብትህ እቀፋቸው የምትለኝ፥ በውኑ ይህን ሕዝብ ሁሉ እኔ ፀነስሁትን? ወይስ ወለድሁትን?
እኔን የሚያገለግለኝ ካለ ይከተለኝ፤ የሚያገለግለኝ እኔ ባለሁበት በዚያ ይኖራልና፤ እኔን የሚያገለግለኝንም አብ ያከብረዋል።
ሽማግሌዎቻችንና የሀገራችን ሰዎች ሁሉ፦ ለመንገድ ስንቅ ያዙ፤ ልትገናኙአቸውም ሂዱ፦ እኛ ባሪያዎቻችሁ ነን፤ አሁንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርጉ በሉአቸው አሉን።
ኢያሱንም፥ “እኛ ባሪያዎችህ ነን፤ ከሩቅ ሀገርም ነን” አሉት። ኢያሱም፥ “እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ?” አላቸው።