2 ነገሥት 10:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረውም የኢዩ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ ኀይሉም ሁሉ፥ የገደለውም ሁሉ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀረው በኢዩ ዘመነ መንግሥት የሆነው፣ ያደረገውም ሁሉ፣ ያከናወነውም ሥራ በሙሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዩ ያደረገው ሌላው ነገርና የጀግንነት ሥራውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዩ ያደረገው ሌላው ነገርና የጀግንነት ሥራውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውም የኢዩ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ ጭከናውም ሁሉ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? |
የቀረውም የኢዮርብዓም ነገር፥ እንዴት እንደ ተዋጋ፥ እንዴትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
አካዝያስ ያደረገው የቀረውም ነገር እነሆ፦ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል። በእርሱም ፋንታ የአክዓብ ልጅ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ።
በዮርዳኖስ ምሥራቅ ያለውን የገለዓድን ሀገር ሁሉ፥ በአርኖን ወንዝ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የጋድንና የሮቤልን የምናሴንም ሀገር፥ ገለዓድንና ባሳንን መታ።
የቀረውም የኢዮአካዝ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ኀይሉም፥ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?