ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”
2 ነገሥት 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሩ እንዲህ አይደለም፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም በላቸው” አለው። ኤልያስም ሄደ፤ እንዲሁም ነገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከተኛህበት ዐልጋ አትነሣም፤ በርግጥ ትሞታለህ።’ ” ከዚያም ኤልያስ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም እግዚአብሔር፥ ‘እነሆ አንተ ትሞታለህ እንጂ አትፈወስም! ከተኛህበት አልጋም አትነሣም! ብሎሃል’ በሉት።” ስለዚህ ኤልያስ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እግዚአብሔር፥ ‘እነሆ አንተ ትሞታለህ እንጂ አትፈወስም! ከተኛህበት አልጋም አትነሣም! ብሎሃል’ በሉት።” ስለዚህ ኤልያስ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም፤” በላቸው’” አለው። ኤልያስም ሄደ። |
ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”
ኤልያስም፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ መልእክተኞችን ለምን ላክህ? በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? እንደዚህ አይደለም፤ ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም” አለው።
እነርሱም፥ “አንድ ሰው ሊገናኘን መጣና፦ ሂዱ፤ ወደ ላካችሁ ንጉሥ ተመልሳችሁ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ትጠይቅ ዘንድ የላክህ በእስራኤል ዘንድ አምላክ ስለሌለ ነውን? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከወጣህበት አልጋ አትወርድም በሉት አለን” አሉት።
በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ታመመ፤ ለሞትም ደረሰ። ነቢዩም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል” አለው።
እነሆ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች እንዲሁ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።
እግዚአብሔር ስለ እነርሱ፥ “በእውነት በምድረ በዳ ይሞታሉ” ብሎ ተናግሮአልና። ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ፥ ከነዌም ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ አንድ ሰው ስንኳ አልቀረም።
እግዚአብሔርም እስራኤልን ከአንተ ጋር በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል፤ ነገም አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ልጆችህ ትወድቃላችሁ፥ እግዚአብሔርም የእስራኤልን ጭፍራ ደግሞ በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል።