የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው ተከትዬ፥ ሁሉንም በየተራው እውነተኛውን እጽፍልህ ዘንድ መልካም ሁኖ ታየኝ።
2 ዮሐንስ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽማግሌው፤ በእውነት ለምወድዳት፣ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ለሚወድዷት፣ ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆቿ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽማግሌው፥ ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆችዋ፥ በእውነት ለምወዳቸው፥ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ለሚወዱአቸው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆችዋ፤ ከእኔ ከሽማግሌው የተላከ መልእክት፤ እኔ በእውነት እወዳችኋለሁ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ይወዱአችኋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ እኔ ሽማግሌው በእውነት ለምወዳቸውና እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ደግሞ ለሚወዱአቸው ለተመረጠች እመቤትና ለልጆችዋ፤ |
የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው ተከትዬ፥ ሁሉንም በየተራው እውነተኛውን እጽፍልህ ዘንድ መልካም ሁኖ ታየኝ።
ነገር ግን ወደ እውነተኛው ወንጌል እግራቸውን እንዳላቀኑ ባየሁ ጊዜ፥ በሰው ሁሉ ፊት ኬፋን እንዲህ አልሁት፥ “አንተ አይሁዳዊ ስትሆን በአይሁድ ሥርዐት ያይደለ፥ በአረማውያን ሥርዐት የምትኖር ከሆነ እንግዲህ አይሁድ እንዲሆኑ አረማውያንን ለምን ታስገድዳቸዋለህ?”
ለምንም ይሆናሉ ብለን የማናስባቸው ናቸው፤ እውነተኛው ትምህርት በእናንተ ይጸና ዘንድ አንዲት ሰዓትም እንኳ አልተገዛንላቸውም።
እናንተ ሰነፎች የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ ለዐይን በሚታየው እውነት እንዳታምኑ ማን አታለላችሁ? እርሱም እንዲሰቀል አስቀድሞ የተጻፈለት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
የእውነት ቃል በሆነው በወንጌል ትምህርት፥ አስቀድሞ ስለ ሰማችሁት፥ በሰማይ ስለ ተዘጋጀላችሁ ተስፋችሁም እንጸልያለን።
እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
አሁንም እመቤት ሆይ! እርስ በርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ፤ ይህች ከመጀመሪያ በእኛ ዘንድ የነበረች ትእዛዝ ናት እንጂ አዲስ ትእዛዝን እንደምጽፍልሽ አይደለም።