2 ቆሮንቶስ 6:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፥ ለእናንተ አፋችን የተከፈተ ነው፤ ልባችንም የሰፋ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፤ ሁሉን በግልጽ ነግረናችኋል፤ ልባችንንም ወለል አድርገን ከፍተንላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ! በግልጽ ነግረናችኋል፥ ልባችንንም ለእናንተ ወለል አድርገን ከፍተንላችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በቆሮንቶስ የምትኖሩ ሰዎች ሆይ! እነሆ፥ በግልጥ ተናግረናችኋል፤ ልባችንንም በሰፊው ከፍተንላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፥ አፋችን ለእናንተ ተከፍቶአል ልባችንም ሰፍቶላችኋል፤ |
ያመለጠውም ሳይመጣ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች፤ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተች፤ ከዚያም በኋላ እኔ ዲዳ አልሆንሁም።
እርሱ አታላይና ኵሩ ሰው ነው፣ በስፍራው ዐርፎ አይቀመጥም፣ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፣ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።
የምኵራብ አለቃ ቀርስጶስም ከነቤተ ሰቡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ፤ ከቆሮንቶስ ሰዎችም ብዙዎች ሰምተው አምነው ተጠመቁ።
እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወጣለሁ፤ ስለ ሕይወታችሁም ሰውነቴን አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እናንተንም እጅግ ብወዳችሁ ራሴን ወደድሁ።
ከብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት የተነሣ በብዙ እንባ ይህን ጽፌላችኋለሁ፤ ነገር ግን እጅግ እንደምወዳችሁ እንድታውቁ ነው እንጂ እንድታዝኑ አይደለም።
እናንተ ሰነፎች የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ ለዐይን በሚታየው እውነት እንዳታምኑ ማን አታለላችሁ? እርሱም እንዲሰቀል አስቀድሞ የተጻፈለት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ሁኛለሁ፤ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እማልዳችኋለሁ፤ አንዳች አልበደላችሁኝምና።
እናንተ የፊልጵስዩስ ሰዎች፤ በመጀመሪያው ትምህርት ከመቄዶንያ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ፥ ከእናንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክርስቲያን በመስጠትም ቢሆን፥ በመቀበል ከእኔ ጋር እንዳልተባበሩ እናንተ ታውቃላችሁ።
ሐናም ጸለየች፤ እንዲህም አለች፦ “ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ ቀንዴም በአምላኬ በመድኀኒቴ ከፍ ከፍ አለ፤ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤ በማዳንህም ደስ ብሎኛል።