ሙሴም ከእርሱ ጋር ይነጋገር ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በገባ ጊዜ እስኪወጣ ድረስ መሸፈኛውን ከፊቱ ያነሣ ነበር፤ በወጣም ጊዜ ለእስራኤል ልጆች የታዘዘውን ነገር ይነግራቸው ነበር።
2 ቆሮንቶስ 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እግዚአብሔር በተመለሱ ጊዜ ግን ያ መጋረጃ ከእነርሱ ይርቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን አንድ ሰው ወደ ጌታ ዘወር ሲል መሸፈኛው ይወገዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሰው ወደ ጌታ ፊቱን ሲያዞር መጋረጃው ይወገዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሰው ወደ ጌታ ሲመለስ “መሸፈኛው ይወገዳል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል። |
ሙሴም ከእርሱ ጋር ይነጋገር ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በገባ ጊዜ እስኪወጣ ድረስ መሸፈኛውን ከፊቱ ያነሣ ነበር፤ በወጣም ጊዜ ለእስራኤል ልጆች የታዘዘውን ነገር ይነግራቸው ነበር።
እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን ዕወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።”
በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙን፥ ሥርዐቱንና ፍርዱን ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ብትሰማ፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ብትመለስ ይባርክሃል።
ይህም ሁሉ ነገር በመጨረሻው ዘመን ይደርስብሃል፤ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔርም ትመለሳለህ፤ ቃሉንም ትሰማለህ።