2 ቆሮንቶስ 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይስ ራሴን በሁሉ ያዋረድሁ በደልሁ ይሆን? እናንተ ከፍ ከፍ ትሉ ዘንድ፥ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያለ ዋጋ አስተምሬአችኋለሁና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ከፍ እንድትሉ ራሴን ዝቅ አድርጌ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያለ ዋጋ ለእናንተ መስበኬ እንደ ኀጢአት ተቈጥሮብኝ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ከፍ እንድትሉ ራሴን ዝቅ አድርጌ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያለ ዋጋ ለእናንተ መስበኬ እንደ ኃጢአት ተቈጥሮብኝ ይሆን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያለ ደመወዝ ለእናንተ መስበኬና እናንተን ከፍ ለማድረግ ራሴን ማዋረዴ ምናልባት እንደ ኃጢአት ተቈጥሮብኝ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ የእግዚአብሔርን ወንጌል ያለ ደመወዝ ስለ ሰበክሁላችሁ፥ እናንተ ከፍ እንድትሉ ራሴን እያዋረድሁ ኃጢአት አድርጌ ይሆንን? |
የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማስተማር ተለይቶ ከተጠራ ሐዋርያ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሚሆን ከጳውሎስ፥
በእኛ ሹመት ሌላ የሚቀድመን ከሆነ የሚሻላችሁን እናንተ ታውቃላችሁ፤ እኔ ይህን አልፈለግሁትም፤ ነገር ግን የክርስቶስን ትምህርት እንዳላሰናክል በሁሉ እታገሣለሁ።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔ ጳውሎስ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ብርቅ ግን የምደፍራችሁ በክርስቶስ የዋህነትና ቸርነት እማልዳችኋለሁ፥ በፍቅራችሁ እታመናለሁና።
አብዝተንም እናስተምራችኋለን፤ ያንጊዜም መጠናችን ከሥራችን ጋር ከፍ ከፍ ይላል፤ እኛስ ቀና ባልሆነውና በማይገባው አንመካም።
እከብድባችሁ ዘንድ ወደ እናንተ ካለመምጣቴ በቀር፥ ከአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያሳነስኋችሁ በምንድን ነው? ይህቺን በደሌን ይቅር በሉኝ።
ወንድሞች ሆይ! ድካማችንና ጥረታችን ትዝ ይላችኋል፤ ከእናንተ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን እየሠራን፥ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ሰበክን።
ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም።