2 ዜና መዋዕል 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድረ በዳም ያለውን ተድሞርን፥ በኤማትም የጸኑ ከተሞችን ሁሉ ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድረ በዳውም ውስጥ ተድሞርንና ቀድሞ በሐማት ሠርቷቸው የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድረ በዳም ያለውን ተድሞርን፥ በሐማትም የሠራቸውን ለግምጃ ቤት የሚያገለግሉትን ከተሞች ሁሉ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በበረሓ የምትገኘውን የታጽሞርን ከተማና በሐማት ያለውን የስንቅና የትጥቅ ማኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ አጠናከረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድረ በዳም ያለውን ተድሞርን፥ በሐማትም የሠራቸውን የዕቃ ቤቱን ከተሞች ሁሉ ሠራ። |
ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ፥ መወርወሪያም የነበራቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ላይኛውን ቤትሖርን፥ ታችኛውንም ቤትሖርን ሠራ።
በብርቱ ሥራም ያስጨንቋቸው ዘንድ የሠራተኞች አለቆችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፌቶምን፥ ራምሴንና የፀሐይ ከተማ የምትባል ዖንን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ።